በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እ.አ.አ. በ2016 የኬንያን ንግድ ችግሮች ሊገጥሙ ይችላሉ ተባለ


ንግድን ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን የሚጠቁም ዓለም አቀፍ ተቋም፥ በያዝነዉ ዓመት 2016 አሸባሪነት፥ ሙስና፣ በፍትሃዊ ፍርድ ስርፃት ጉድለትና በመጪዉ አጠቃላይ ምርጫ ምክንያት የኬንያ ንግድ ችግሮች ሊገጥሙት እንደሚችል ገለጸ።

ግሎባል ቢዝነስ ሪስክ ኮንትሮል ኮንሳልተንሲ "Global Business Risk Control Consultancy" ማለትም ንግድን ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን የሚጠቁመዉ ዓለም አቀፍ ተቋም ዛሬ ናይሮቢ ዉስጥ የፋ ባደረገዉ ዘገባ በ2016 ዓም የሕዝባዊ ድርጅቶች ንግዶችን ሊያጋጥሙ የሚችሉ ዓለም አቀፍ ችግሮችን ለይቶ በማዉጣት ነዉ።

የተቋሙ የምስራቅ አፍሪቃ የንግድ ገምጋሚ ፖል ጋብርኤል(Paul Gabriel) ምስራቅ አፍሪቃ በአሸባሪነት እየተጠቃ ነዉ የሚለዉ ግምት ወይም አመለካከት የክልሉን የንግድ ማህበረሰቦች ማለትም ኢኮኖሚ በአሉታዊነት እያጠለመ ነዉ ብለዋል።

ንግዶችን ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን የሚገመግመዉ የኮንትሮል ሪስክ (Control Risk) ባለሙያ በኬንያ መጪዉን የእአአ 2017 ምርጫ ምክንያት በማድረግ ጸረ ሙስንና የተመለከቱ ንግግሮችም በብዛት መሰማት ጀምረዋል፣ በሌላ በኩል ግን በንግዱና ፓለቲካዉ ዙሪያ የሚታዮ ሙስናን የማጥፋት ፍላጎቶች፣ ሂደት እንደማያሳዩና ያዘገሙ መሆናቸዉን ተናግረዋል።

ንግድን ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን የሚጠቁም ዓለም አቀፍ ተቋም ሰራተኞች
ንግድን ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን የሚጠቁም ዓለም አቀፍ ተቋም ሰራተኞች

በተቋሙ ዘገባ መሰረት ዓለም አቀፍ ንግድን የገጠሙ አደጋዎች አሸባሪነት፣ ሶሪያ ዉስጥ የሰፈነዉ ቀዉስ ፣ ኢንተርነትን በመጠቀም የሚፈጸሙ ወንጀሎ እንዲሁም የአዉሮፓ ሕብረት መጨዉ እድል በእርገጠኝነት ያለመታወቁ ናቸዉ።

የድምጽ ፋይሉን በመጫን ትዝታ በላቸዉ ያቀረበችዉን ዘገባ ያድምጡ።

በእ.አ.አ2016 የኬንያን ንግድ ችግሮች ሊገጥሙ ይችላሉ ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:18 0:00

XS
SM
MD
LG