በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሊያና ደቡብ ሱዳን የረዷቸውን አመሠገኑ


የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኦማር አብዱል ራሺድ አሊ ሸርማርኬ ና የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንቷ ጄምስ ዋኒ አጋ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰባኛ ጠቅላላ ጉባዔ ንግግር ሲያደርጉ - መስከረም 20/2008 ዓ.ም፤ ኒው ዮርክ
የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኦማር አብዱል ራሺድ አሊ ሸርማርኬ ና የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንቷ ጄምስ ዋኒ አጋ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰባኛ ጠቅላላ ጉባዔ ንግግር ሲያደርጉ - መስከረም 20/2008 ዓ.ም፤ ኒው ዮርክ

በደቡብ ሱዳን ጦርነቱ ቆሞ ሰላም ማግኘታቸውን ምክትል ፕሬዚዳንቷ ጄምስ ዋኒ አጋ አስታውቀዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የዛሬዋ ሶማሊያ ትናንት የምታውቋት አይደለችም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ኦማር አብዱል ራሺድ አሊ ሸርማርኬ ተናግረዋል፡፡

ሶማሊያና ደቡብ ሱዳን የረዷቸውን አመሠገኑ
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:00 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በደቡብ ሱዳን ጦርነቱ ቆሞ ሰላም ማግኘታቸውን ምክትል ፕሬዚዳንቷ ጄምስ ዋኒ አጋ አስታውቀዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የዛሬዋ ሶማሊያ ትናንት የምታውቋት አይደለችም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ኦማር አብዱል ራሺድ አሊ ሸርማርኬ ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ መሪዎች እነዚህን ካለፉ ቀናት የተሻለ ቀን ብሥራት የተናገሩት ኒው ዮርክ በመካሄድ ላይ ባለው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰባኛ ጠቅላላ ጉባዔ ለተሰበሰቡ የዓለም መሪዎች ነው፡፡

ሁለቱም መሪዎች በክፉ ቀኖቻቸው ከጎናቸው የቆሙ የአፍሪካና ከዚያም ባሻገር ያሉ አጋሮቻቸውን በየንግግሮቻቸው ላይ አመስግነዋል፡፡

ሁለቱም መሪዎች ከፊታቸው የተደቀኑ ቀሪ ፈተናዎችን ተናግረዋል፡፡

የሶማሊያው ሻርማርኬ “አልሻባብን አሸንፈናል፤ ሞቃዲሾ ውስጥ የሚሰማው የጥይት ድምፅ ቀንሷል” ብለዋል፡፡ ግን በመሠረተ-ልማት ግንባታና በሌሎችም የልማት መስኮች የሚጠብቃቸውን ብርቱ ሥራ ጠቁመው አጋሮቻቸው ከጎናቸው እንዳይለዩ ጠይቀዋል፡፡

የደቡብ ሱዳኑ ኢጋም እንዲሁ የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላም ቢሆን አንዳንድ ቀሪ ችግሮች አሉባቸው ያሉባቸውን አካባቢዎች ጠቁመዋል፡፡

ለሙሉው የምንያ አፈወርቂ የኒው ዮርክ ዘገባ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG