በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬታጂ ብራውን ጃክሰን የጠቅላይ ፍ/ቤት ዳኝነት ጸደቀ


ዳኛ ኬታጂ ብራውን ጃክሰን
ዳኛ ኬታጂ ብራውን ጃክሰን

የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ዛሬ ከቀትር በኋላ በሰጠው ድምፅ የዳኛ ኬታጂ ብራውን ጃክሰንን ሹመት ሃምሳ ሦስት ለአርባ ሰባት በሆነ የድምፅ ብልጫ በዛሬው ዕለት አጽድቆላቸዋል።

ሪፐብሊካኖች እና ዲሞክራቶች እኩል መቀመጫ በያዙበት የህግ መወሰኛው ምክር ቤት ዲሞክራቶች ከምክትል ፕሬዚደንቷ ድምጽ ጋር አብላጫ ድምጽ አላቸው። ሦስት ሪፐብሊካን ሴኔተሮች ሱዘን ኮሊንስ፣ ሊሳ መርኮውስኪ እና ሚት ሮምኒ የዳኛ ጃክሰንን ዕጩነት እንደሚደግፉ ማስታወቃቸው ይታወሳል።

የሀምሳ አንድ ዓመቷ የፌዴራል የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ዳኛ ኬታጂ ብራውን ጃክሰን በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ታሪክ የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት እንዲሁም ሦስተኛ ጥቁር ዳኛ ይሆናሉ።

ባሁኑ ወቅት ሶስት ሴት ዳኞች ሶኒያ ሶቶማዮር፣ ኤሌና ኬገን እና ኤሚ ኮኒ ባረት በጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኝነት እያገለገሉ ሲሆን ዳኛ ጃክሰን ሲጨመሩ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ባንድ ጊዜ አራት ሴት ዳኞች ሲኖሩት የመጀመሪያ ጊዜ ይሆናል።

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ኬታጂ ብራውን ጃክሰንን ጡረታ በሚወጡት ዳኛ ስቴፈን ብሬየር ቦታ እንዲተኩ ያጩዋቸው ሲሆን በጋው ወራት ላይ ዳኛ ብሬየር ሲሰናበቱ ወንበራቸውን ይረከባሉ።

XS
SM
MD
LG