በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለጠ/ፍርድ ቤት ዳኝነት የታጩት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት እየቀናቸው ነው


የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የጠ/ፍ/ቤት ዳኛ ሆነው የታጩት ዳኛ ከታንጂ ብራዎን ጃክሰን
የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የጠ/ፍ/ቤት ዳኛ ሆነው የታጩት ዳኛ ከታንጂ ብራዎን ጃክሰን

ለዩናይትድ ስቴትስ የመጀመሪያዋ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ለመሆን የታጩት የአቤቱታ ሰሚው ፍርድ ቤት ዳኛ ከታንጂ ብራወን ጃክሰን፣ ትናንት ሰኞ ሹመታቸው እንዲጸድቅ ያግዛል የተባለውን የመጀመሪያውን ድጋፍ ማግኘታቸው ተገለጸ፡፡

ዕጩ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛዋ ድጋፉን ያገኙት በዚህ ሳምንት መጠናቀቂያ ላይ ለህግ መወሰኛው ምክር ቤት ያቀርባቸዋል ከተባለው የምክር ቤቱ የሴኔት ኮሚቴ አባላት መካከል መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ከፍተኛውን ፍርድ ቤት እንዲያገለግሉ በፕሬዚዳን ጆ ባይደን የታጩት ብራወን ትናንት ሰኞ ከወዲሁ የሁለት ሪፐብሊካን አባላትን ድጋፍ ማግኘታቸው ተገልጿል፡፡

የህግ መወሰኛው ምክር ቤት አባላት የሆኑት ሴንተር ሊዛ መርካውስኪና ሴነተር ሚት ራምኒ የጃክሰንን ዕጩነት በመደገፍ ድምጻቸው እንደሚሰጡ አስታውቀዋል፡፡

ባለፈው ሳምንትም የሪፐብሊካን አባል የሆኑት ሱሳን ኮሊንስ ለጃክሰን ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ ማስታወቃቸው ይታወቃል፡፡ እንዲህ ብለዋል ኮሊንስ

“ዳኛ ጃክሰንን የህይወትና የአገልግሎት ታሪክ ለማወቅ ብዙ ጊዜ ወስጃለሁ፡፡ በኮሚቴው ፊት ለምስክርነት ከመቅረባቸው በፊትና ከቀረቡም በኋላ ሁለት ሰዓት ለፈጀ ጊዜ ሁለት ጊዜ ቃለ መጠይቅ አድርጌያቸዋለሁ፡፡ ሌሎች የህግ ባለሙያዎችን አነጋግሬያለሁ፤ በርካታ ሰነዶችን ተመልክቻለሁ፡፡ በመጨረሻም ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኝነት የምንፈልገውን ብቃትና ማረጋገጫ የሚያሟላ ልምድና ብቃት አላቸው ብዬ ወስኛለሁ፡፡”

የሦስቱ ሪፐብሊካን ድምጾች 48 ከሚሆኑት ዴሞክራቶችና ከሁለት ገለልተኛ የምክር ቤት አባላት ጋር ተደምሮ፣ ምክር ቤቱ በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ ለመጀመሪያዋ ጥቁር አፍሪካ አሜሪካዊ ሴት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኝ እንዲሆኑ ለመወሰን ከበቂ በላይ ድምጽ ያለው መሆኑ ተመልክቷል፡፡

የህግ መወሰኛው ምክር ቤት አባላት በሚቀጥለው ሳምንት ለፋሲካ በዓል እረፍት ከመውሰዳቸው በፊት ተነጋግረውበት የመጨረሻውን ድምጽ ይሰጡበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የህግ መወሰኛው ምክር ቤት አባላት በሚቀጥለው ሳምንት ለፋሲካ በዓል እረፍት ከመውሰዳቸው በፊት ተነጋግረውበት የመጨረሻውን ድምጽ ይሰጡበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

XS
SM
MD
LG