በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዳኛ ኬታጂ ብራውን ጃክሰን የጠቅላይ ፍ/ቤት ሹመት ዛሬ ይጸድቅላቸዋል ተብሎ እየተጠበቀ ነው


የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የጠ/ፍ/ቤት ዳኛ ሆነው የታጩት ዳኛ ኬታጂ ብራውን ጃክሰን
የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የጠ/ፍ/ቤት ዳኛ ሆነው የታጩት ዳኛ ኬታጂ ብራውን ጃክሰን

በህግ መወሰኛ ምክር ቤቱ የብዙሃኑ ዲሞክራቶች መሪ ሴኔተር ቸክ ሹመር ናቸው ትናንት ምሽት በሰጡት ቃል ምክር ቤቱ ዛሬ ከቀትር በኋላ የመጨረሻውን ድምፅ ሊሰጥበት ዕቅድ መኖሩን ያስታወቁት።

ሪፐብሊካኖች እና ዲሞክራቶች ዕኩል መቀመጫ በያዙበት የህግ መወሰኛው ምክር ቤት ዲሞክራቶች ከምክትል ፕሬዚዳንቷ ድምፅ ጋር አብላጫ ድምፅ አላቸው። ሦስት ሪፐብሊካን ሴኔተሮች ሱዘን ኮሊንስ፣ ሊሳ መርኮውስኪ እና ሚት ሮምኒ የዳኛ ጃክሰንን ዕጩነት ደግፈው ድምፅ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል።

የሀምሳ አንድ ዓመቷ የፌዴራል የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ዳኛዋ ኬታጂ ብራውን ጃክሰን ሹመታቸው ከጸደቀ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ታሪክ የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ዳኛ ይሆናሉ።

ባሁኑ ወቅት ሦስት ሴቶች ዳኛ ሶኒያ ሶቶማዮር ዳኛ ኤሌና ኬገን እና ዳኛ ኤሚ ኮኒ ባረት በጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኝነት እያገለገሉ ሲሆን ዳኛ ጃክሰን ከተጨመሩ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ባንድ ጊዜ አራት ሴት ዳኞች ሲኖሩት የመጀመሪያ ጊዜ ይሆናል።

XS
SM
MD
LG