በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የጠ/ፍ/ቤት ዳኛ ሆነው የታጩት ጃክሰን ምስክርነት ተጠናቀቀ


የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የጠ/ፍ/ቤት ዳኛ ሆነው የታጩት ዳኛ ከታንጂ ብራዎን ጃክሰን
የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የጠ/ፍ/ቤት ዳኛ ሆነው የታጩት ዳኛ ከታንጂ ብራዎን ጃክሰን

የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው በፕሬዚዳንት ባይደን የታጩት የዳኛ ከታንጂ ብራዎን ጃክሰን፣ በህግ መወሰኛው ምክር ቤት ፊት ቀርበው የሚሰጡት የምስክርነት ቃል በትናንትናው እለት አራተኛውንና የመጨረሻውን ቀን አሳልፏል፡፡

ሂደቱን የተከታተሉ የህግ ባለሙያዎች ጃክሰን ለታጩበት የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኝነት ብቃታቸውን ያረጋግጡበት ምስክርነት መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡

ለአራት ቀናትና ሰላሳ ሰዓታት ብቃታቸው ሲፈተንበት በቆየው የምክር ቤቱ ውሎ ከአሜሪካ የጠበቆች ማህበርና ከሌሎች ባለሙያዎች የተሰማውን ምስክርነት ተንተርሶ ከኮሚቴው ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ጃክሰን አጥጋቢና የላቀ ምላሽ መስጠታቸው ተነግሮላቸዋል፡፡

አብዛኞቹ የሪፐብሊካን አባላት ጃክሰን በወንጀለኞች ላይ የሚያስተላልፏቸው ውሳኔያዎች ለዘብ ያሉ ናቸው በሚለው መከራከሪያ ላይ ብዙ ማጥፋታቸው ተመልክቷ፡፡

የህግ ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን የመንግሥት ባለሥልጣናትና የሰብዊ መብት ተሟጓቾች ድጋፋቸውም ስጥተዋቸዋል፡፡ የምክር ቤቱ ኮሚቴ ውሳኔውን እኤአ ሚያዚያ 4 የሚያሳውቅ ሲሆን ምክር ቤቱም ከፋሲካ በፊት ድምጽ ይሰጥበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ሹመቱ ከጸደቀላቸው ከታንጂ ብራውን ጃክሰን በዩናዩትድስ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ታሪክ የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ይሆናሉ፡፡

XS
SM
MD
LG