በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የጠቅላይ ፍ/ቤት ዕጩ በመወሰኛው ም/ቤት


ለዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የታጩት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ዳኛ፣ የከታንጂ ብራዎን ጃክሰን
ለዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የታጩት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ዳኛ፣ የከታንጂ ብራዎን ጃክሰን

የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛው የፍትህ ኮሚቴ፣ ለዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የታጩትን የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ዳኛ፣ የከታንጂ ብራዎን ጃክሰንን ታሪካዊ ሹመት አስመልክቶ የምስክርነት ቃል ከዛሬ አንስቶ መስማት እንደሚጀምር ተነግሯል፡፡

በምክር ቤቱ የጠባብ ድምጽ ብልጫ ያላቸው ዴሞክራቶች፣ ከመጭው የፋሲካ በዓል ወዲህ ሹመቱን ማጽደቅ የሚፈልጉ ሲሆን፣ የ51 ዓመቷ የፌዴራል ዳኛ ጃከስን ባለፉት 9 ዓመታት የፈጸሙት ጉልህ ሥህተት ካለም መከላከል ይጠበቅባቸዋል፡፡

ጃክሰን ለሥራው ብቁ መሆናቸውን ለመግለጽ ራሳቸውን የሚያስተዋውቁበትን የመክፈቻ ንግግራቸውን ዛሬ ሰኞ ከሰዓት በኋላ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የኮሚቴው 11 ዴሞክራትና 11 የሪፐብሊካን ምክር ቤት አባላትም ለሚያቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡

የሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ምሩቅ ጃክሰን በፌዴራሉ መንግሥት የሁለት ዓመት የህዝብ ተከላካይ ጥብቅና አገልግሎታቸውን ጨምሮ ራሳቸውን በማስተዋወቅ የሚያሰሙት ንግግርና ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች የሚሰጡት ምላሽ በርካታ አሜሪካውያንና የህግ መወሰኛው ምክር ቤት አባላት የበለጠ እንዲረዷቸው ያደርጋል የሚል ግምት ማሳደሩን ተመልክቷል፡፡

ሹመቱ ከጸደቀላቸው በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የመጀመሪያው ጥቁር ሴት ሲሆኑ ከማርሻል እና እሳቸውን ከተኩት ክላረንስ ቶማስ ቀጥሎ ሦስተኛዋ ጥቁር እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡

እጩ ዳኞችን የሚገመግመው የአሜሪካ ጠበቆች ማኅበር ባላፈው ዓርብ ጃክሰን ከፍተኛ የብቃት ደረጃ ያላቸው መሆኑን በሰጠው ሙሉ ድምፅ አረጋግጧል፡፡

XS
SM
MD
LG