በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕላቲኒ ለዓለም እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ፕሬዘዳንት ምርጫ እንደማይወዳደሩ አስታወቁ


የአውሮፓ እግር ኳስ ፌዴሽን ፕሬዘዳንት ፕላቲኒ (Platini)ፋይል ፎቶ
የአውሮፓ እግር ኳስ ፌዴሽን ፕሬዘዳንት ፕላቲኒ (Platini)ፋይል ፎቶ

”ጊዜው ለኔ አመቺ አይሆንም፥ ከሌሎቹ እጩ ተወዳዳሪዎች ጋርም በእኩል ደረጃ ዘመቻ ማካሄድ አልችልም” ብለዋል ፕላቲኒ (Platini)

ባንድ ወቅት የታገዱትን የፊፋ ፕሬዘዳንት ይተካሉ ተብለው በስፋት ግምት የተሰጣቸው ሚሸል ፕላቲኒ (Michel Platini)በመጪው የካቲት ለዓለም እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ፕሬዘዳንት ምርጫ እንደማይወዳደሩ አስታወቁ።

የታገዱት የአውሮፓ እግር ኳስ ፌዴሽን ፕሬዘዳንት ፕላቲኒ (Platini) ዛሬ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፥ ለስምንት ዓመት የተጣለባቸው እገዳ ቢነሳላቸው እንኳ፥ ከምርጫው በፊት የተዋጣለት ዘመቻ ማካሄድ እንደማይችሉ አስረድተዋል።

”ጊዜው ለኔ አመቺ አይሆንም፥ ከሌሎቹ እጩ ተወዳዳሪዎች ጋርም በእኩል ደረጃ ዘመቻ ማካሄድ አልችልም” ብለዋል ፕላቲኒ (Platini) አክለውም።

ሚሸል ፕላቲኒ (Michel Platini)ፕሬዘዳንቱን ሰፕ ብላተርን (Sepp Blatter) ለመተካት የነበራቸው ሕልም የተበላሸው፥ እ አ አ በ 2011 ዓ.ም. ብላተር ሁለት ሚሊዮን ዶላር ለ Platini በጉቦ መልክ ከፍለዋል የሚል የሙስና ክስ ከቀረበባቸው በሁዋላ መሆኑ ይታወቃል።

ያን ክፍያ በተመለከተ የስዊዘርላንድ ዓቃብያና ሕግ የወንጀል ምርመራ ከፍተዋል። የዜና ዘገባውን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።

ፕላቲኒ ለዓለም እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ፕሬዘዳንት ምርጫ እንደማይወዳደሩ አስታወቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:13 0:00

XS
SM
MD
LG