ትልቁ የዓለም የእግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ኅብረት - ፊፋ (FIFA) በሙስና ቅሌት መዘፈቁ ይፋ የሆነ ሰሞን፣ ፕሬዚደንቱ ደግሞ ለአምስተኛ ጊዜ ለመመረጥ እየተሰናዱ መሆናቸው ተሰማና፣ ሁሉም «... አሁን ማ ይሙት..» ይል ነበር። ግን ተወዳደሩና ተመረጡ ተባለ። «አጃኢብ» ብለን ሳናበቃ፣ «ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለቀቁ» የሚለው የሚዲያው ሁሉ አርዕስተ-ዜና ሆነ። አከታትሎም፣ «ኧረ እንዲያውም በሙስና ተጠርጥረዋል፣ የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል ምርመራ ቢሮ - ኤፍቢአይም እየተከታተላቸው ነው» ተባለ። አዪ….
በሌላ በኩል ደግሞ “ሀገሬ በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር በ2010 ዓ.ም የተካሄደውን የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ለማዘጋጀት ስትል ለፊፋ ጉቦ አልሰጠችም ሲሉ የደቡብ አፍሪካ የስፖርት ሚኒስትር ፊኪሌ ምባሉላ ተናግረዋል።
ድርጅቱ በሙስና ቅሌት ተወጥሮ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ሥልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው የለቀቁትን ብላተርን እንደሚያደንቁም ሚኒስትሩ አክለው አመልክተዋል።
ለመሆኑ የኳስ አዋቆች፣ በተለይም ፊፋን በውል የሚያውቁ ምን ይሉ ይሆን? የሚለው ትኩረታችንን ሳበና የኳስ ሰዎችን ማፈላለግ ቀጠልን። እኒህን ሰው፣ ሴፕ ብላተርን ማለታችን ነው፣ ከይድነቃቸው ተሰማ ቤተሰብ የበለጠ የማያውቅ የለም አልንና ትልቁን ልጃቸውን ታደለ ይድነቃቸውን ጠየቅን፣ «ምን ጉድ ነው ይሄ ነገር አቶ ታደለ?» ስንል…
ከጆሃንስበርግ የደረሰንን ዘገባና ከአቶ ታደለ ይድነቃቸው ጋር የተደረገውን ቃለምልልስ ያዳምጡ