በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም አቀፍ የኳስ ጨዋታ ፌድደረሽን ምክትል ፕረዚዳንቶች ታሰሩ


ፊፋ (FIFA) ማለት የዓለም አቀፍ የኳስ ጨዋታ ፌድደረሽን
ፊፋ (FIFA) ማለት የዓለም አቀፍ የኳስ ጨዋታ ፌድደረሽን

የፊፋ ባለስልጣኖች ዛሬ በዙሪክ ፍርድ ቤት ከቀረቡ በኋላ አልፍረዶ ሃዊት (Alfredo Hawit) እና ጅዋን ኣንግል ናፑት (Juan Angel Napout) እንደታሰሩ ተገልጿል።

የስዊትዘርላንድ የፍርድ ሚኒስቴር የፊፋ (FIFA) ማለት የዓለም አቀፍ የኳስ ጨዋታ ፌድደረሽን ምክትል ፕረዚዳንቶች አልፍረዶ ሃዊት (Alfredo Hawit) እና ጅዋን ኣንግል ናፑት (Juan Angel Napout) እንደታሰሩ ዛሬ ገልጿል። ኢላማ ሲደረጉ ከቆዩት የፊፋ ባለስልጣኖች ውስጥ ተፈረጁ ማለት ነው።

ሁለቱ ሰዎች ዛሬ ዙሪክ ውስት ፍርድ ቤት በቀረቡበት ወቅት ወደ ዩናትድ ስቴትስ (United States) የመላኩን ጉዳይ እንደተቃወሙ የፍርድ ሚኒስቴሩ ገልጿል። United States ሁለቱ ሰዎች በሚልዮኖች ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ጉቦ ሳይቀበሉ አይቀርም የሚል ጥርጣሩ እንዳላት የስዊዝ ባለስልጣኖች አመላክተዋል።

የሁንዱራስ ተወላጅ የሆኑት የሰሜን አሜሪካ፣ የማዕከላዊ አሜሪካና የካሪብያን የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ፕረዚዳንት ናቸው። የፓራጓይ ተወላጅ የሆኑት ናፑት (Napout) ደግሞ የደቡብ አሜሪካ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ፕረዚዳንት ናቸው።

ሁለቱ ባለስልጣኖች አሁን የታሰሩት በፊፋ ከታየው የሙስና ቅሌት ጋር በተያያዘ እንዲያዙ ዩናይትድ ስቴትስ (United States) በጠየቀችው መሰረት ነው።

የዓለም አቀፍ የኳስ ጨዋታ ፌድደረሽን ምክትል ፕረዚዳንቶች ታሰሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:26 0:00

XS
SM
MD
LG