በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያ ከተሞች የሚካሄድ ተቃዉሞ ቀጥሏል


ተቃዋሚዎቹ፣ የታሰሩ እንዲፈቱ ለተገደሉት ሰዎች ቤተሰቦች ካሳ እንዲከፈል የሚል መፈክር እያሰሙ መሆናቸው ከቦታው የደረሱን ዘገባዎች ይገልጻሉ
ተቃዋሚዎቹ፣ የታሰሩ እንዲፈቱ ለተገደሉት ሰዎች ቤተሰቦች ካሳ እንዲከፈል የሚል መፈክር እያሰሙ መሆናቸው ከቦታው የደረሱን ዘገባዎች ይገልጻሉ

የአዲስ አበባና የፊንፊኔ ዙሪያ የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ተከትሎ በኦሮሚያ ከተሞች ከሕዳር ወር አጋማሽ ጀምሮ ሲካሄድ የነበረዉ ተቃዉሞ ዛሬም በአንዳንድ አካባቢዎች ቀጥሏል። ተቃዋሚዎቹ፣ የታሰሩ እንዲፈቱ ለተገደሉት ሰዎች ቤተሰቦች ካሳ እንዲከፈል የሚል መፈክርም ጨምረዋል።

ተቃዋሚዎቹ እቅዱ ገበሬዎችን አፈናቅሎ መሬት አልባ ያደርጋል፣ የኦሮሞን ባህልና ቋንቋ ያጠፋል ይላሉ። በገዢዉ ፓርቲ ባለስልጣናት የተቀናጀ ማስተር ፕላን ስራ ላይ መዋሉን አስተባብለዋል። ባለፈዉ ታህሳስ አራት ሮይተርስ እንደዘገበዉ ፥ ባለስልጣኖች በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ የእርሻ መሬቶችን እንደ አዲስ ዞን ማቀናጀት መዋለ ንዋይ አፍሳሾችን ይማርካል ማለታቸዉን ጠቅሷል።

በእምራብ ሃረርጌ በአዳ ቡልቱም ወረዳ በዴሳ ከተማ ዛሬ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ ሕብረተሰቡ ”ባርነት በቃን” የሚል መፈክር አንግቦ ለተቃዉሞ እንደወጣ መንግስት ጥቃት እንዳያደርስብኝ ሰሜ አይገለጥ ያሉ የሰልፉ ተካፋይ ለአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ክፍል ገልጸዋል

በቀለ ገርባና በቀለ ነጋ ይፈቱ ፣ የታሰሩ ተማሪዎች ሁሉ ይፈቱ ማስተር ፕላን ይሰረዝ የሚል በራሪ ወረቀቶች ይዘዉ ነዉ የወጡት። መንግድ ላይ የከተማዋ ካቤኒ አባል መሃመድ ሰይድ መጥቶ ወረቀቶችን ከእጃቸዉ ነጥቆ ሲበትን ሰልፈኞቹ ደበደቡት። ፌዴራል ፓሊሶችና አዳማ በታኝ ሃይሎች አሁን ያገኙትን ሁሉ እያወከቡና እያሰሩ ነዉ ፣ አግአዚዎችም ገብተዋል።

የባዴሳ ከተማ ካቢኔ አባል አቶ መሃመድ ሰይድ የበኩላቸዉን እንዲገልጹልን ሰልክ ደዉለንላቸዉ ነበር አያነሱም።

በበምእራብ ሃረርጌ ሂርና ከተማ ለአንድ ሳምንት ያክል ሲካሄድ የሰነበተዉ ተቃዉሞ የመከላከያ ሰራዊት አባላትና አድማ በታኞች በወሰዱት እርምጃ ወደ ለየለት ጦርነት ተቀይሯል ይላሉ ስማቸዉ እንዳይጠቀስ በመጠየቅ የኦሮሚኛ ቋንቋ ክፍልን ያነጋገሩ የሰልፉ ተካፋይ።

"ሰላማዊ ሰልፍ ነበር የተጀመረዉ። መከላከያ ሰራዊት አምጥተዉ በሰላም የጀመርነዉ ትግላችንን ወደ ጦርነት ቀየሩት። በጥይትና በእንባ አስመጪ ጋዝ እየደበደቡን ነዉ። አጋአዚ ሁሉ አምጥተዉ ወንድ ሴት ሳይሉ በሒርና ከተማ ያለ ነዋሪ በር ሰብረዉ በመግባት እያሰሩ እየገረፉ ነዉ" ብለዋል።

በዛሬዉ የጸጥታ ሃይሎች ጥቃት ቁጥራቸዉ በዉል የማይታወቅ ሰዎች ቆስለዋል ብለዋል የሰልፉ ተካፋይ ነኝ ያሉት የዓይን እማኝ። ካሁን በፊት በጽኑ የቆሰሉ ሶስት ሰዎች ጭሮ ሆስፒታል እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የሂርና ከተማ ከንቲባ አቶ ከድር አቦዶ በበኩላቸዉ ከተማዋ ሰላም ናት ይላሉ።

"አይ እየታሰሩ ያሉ ሰዎች የሉም። ዉሸት ሊሆን ይችላል፣ እስካሁን የታሰረ ሰዉ የለም ከተማችን እስካሁን ሰላም ናት፥ ይህ ሁሉ ዉሸት ነዉ" ብለዋል።

ትላንት በምእራብ ሃረርጌ የአሰቦት ከተማ ተማሪዎች የከተማዋ ባንክ ቤት ፊት ለፊት ቆመዉ የአዲስ አበባና የፊንኒኔ ዙሪ የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተቃዉሞ ማሰማታቸዉን የቪኦኤ የአፋን ኦሮሞ ክፍል ባልደረቦች ሰልፉን የተካፈትን በማነጋገር ዘግቧል።

የከተማዋ ፖሊሶችን ባለስልጣናት ተኩስ በማሰማት ሰልፉን መበተናቸዉም ታዉቋል፣ የቆሰለ ሰዉ ግን የለም። የአፋን ኦሮሞ ክፍልን ያነጋገረ አንዱ ተማሪ በአሰቦት ከሰዓት በሁዋላ ከ6- 9 ሰዓት ሁለተኛ ዙር በተካሄደ ተቃዉሞ ላይ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ነጋዴዎች ለገበያ የወጡ አርሶ አደሮች መቀላቀላቸዉን ገልጿል።

”ከዚያ በሁዋላ ሶስት መኪና ሙሉ የመከላከያ አባላት ወደ ከተማዋ ገብተዉ ተኩስ ከፈቱ፥ ተኩስን በመጋፈጥ ተማሪዎቹና ሕዝቡ ድንጋይ በመወርወር ተከላከል በተወረወሩ ድንጋዮች የተጎዱ የመከላከያ አባላት አሉ” በማለት በከተማዋ የነበረዉን ሁኔታ አብራርቷል። ተከትሎም የጸጥታ ሃይሎች ቤቶችን ሰብረዉ ገብተዉ ተማሪዎችን ለቅመዉ አስራዋል ብሏል።

ትናንት በዚሁ በምእራብ ሃረርጌ ጡጢሲ በሚባል ከተማና የዳሮ ገጠር ነዋሮዎች የተቃዉሞ ስልፍ ማከሃዳቸዉን ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ የከተማዉ ነዋሪ ገልጿል። ጥያቄአቸዉም "አቶ በቀለ ገርባ እና የታሰሩት ሁሉ ይፈቱልን ኦሮሞ የሃገር ባለቤት ነዉ በማለት ሴት ወንድ ሳይል ነዉ ሁሉም ለተቃዉሞ የወጣዉ። ተማራዎች አልተካፈሉም። አርሶ አደሮች የአገር ሽማግሌዎች ናቸዉ ልጆቻችንን አትሰሩብን" በማለት ለተቃዉሞ የወጡት።

በጡጢሲ ተቃዉሞዉ በሰላም ቢጠናቀቅም፣ ፖሊሶች ብዙዎችን ቁጥጥር ስር እንዳዋሉ ተገልጾል።

የምእራብ ሃረርጌ አስተዳዳሪ አቶ አልይ ኡመር የአሰቦት ከተማ ከንቲባ አቶ ቶፈቅ አልህ እና የከተማዋ ሰላምና መረጋጋት ሃላፊ አቶ አደም ሲራጅን ለማነጋግር የተደረገዉ ሙከራ አልተሳካም።

የኢትዮጵያ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ ጌታቸዉ ረዳ በኦሮሚያ ሰላማዊ ሰልፍ እንደተጀመረ፣ ተቃዋሚዎቹ የታጠቁና የመንግስት ባለስልጣናናርን መሳሪያ ያልያዙ የጸጥታ ሃይሎችን፣ ገበሬዎችንና፣ ሕዝብን የሚያሸብሩ ናቸዉ ማለታቸዉን ሮይተርስ ባለፈዉ ታህሳስ አራት ዘገባዉ ጠቅሷል።

ዛሬና ትናንት በአንዳንድ ከተሞች ስለተካሄዱ ተቃዉሞዎችን ከመንግስት ጸጥታ አስከባሪዎች ሰለወሰዱት እርምጃ የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ባልደረቦች ያጠናቀሩትን ትዝታ በላቸዉ ታቀርባለች፣ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።

በኦሮሚያ ከተሞች የሚካሄድ ተቃዉሞ ቀጥሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:44 0:00

XS
SM
MD
LG