በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦሮምኛ ተናጋሪ አብያተ ክርስቲያን ኅብረት ጥያቄዎቹን አቀረበ


በፓስተር ዶ/ር ገመቹ ኦላና የተመራው የኦሮሞ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን ኅብረት ልዑካን ቡድን
በፓስተር ዶ/ር ገመቹ ኦላና የተመራው የኦሮሞ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን ኅብረት ልዑካን ቡድን

የኦሮሞ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን ኅብረት መሪዎች ሰሞኑን ዋሺንግተን ዲሲ ተገኝተው ከኢትዮጵያ አምባሣደር አቶ ግርማ ብሩና ከዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤትና ከውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ባለሥልጣናት ጋር ተወያይተዋል፡፡

የኦሮምኛ ተናጋሪ አብያተ ክርስቲያን ኅብረት ጥያቄዎቹን አቀረበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:26 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የኦሮሞ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን ኅብረት መሪዎች ሰሞኑን ዋሺንግተን ዲሲ ተገኝተው ከኢትዮጵያ አምባሣደር አቶ ግርማ ብሩና ከዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤትና ከውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ባለሥልጣናት ጋር ተወያይተዋል፡፡

የኅብረቱ ፕሬዚዳንት ፓስተር ዶ/ር ገመቹ ኦላና ለቪኦኤ በሰጡት ቃል በዩናይትድ ስቴትስ፣ ካናዳ፣ አውሮፓና ሌሎችም የዓለም ክፍሎች የሚገኙ የኦሮሞ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን ኅብረት መሪዎች ጥያቄዎቻቸውን ለባለሥልጣናቱ በፅሁፍ ማቅረባቸውን አመልክተዋል፡፡

የመሪዎቹ ጥያቄዎች ኦሮምያ ውስጥ የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን እና ከኦሮምያ ክልል ልዩ ጦር በአስቸኳይ እንዲወጣ፣ በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ መንግሥቱ እየተጠቀመ ያለውን ከመጠን ያለፈ ኃይል እንዲያቆም፤ ነፃና ገለልተኛ አካል ተቋቁሞ መሣሪያ ያልያዙ ተቃዋሚዎች የተገደሉበት ሁኔታ በጥልቀት እንዲጣራ፤ ሰዎች ለተገደሉበት ኃይል ተጠያቂ በሆኑ ሰዎች ላይ የወንጀል ክሥ እንዲከፈት፤ ያለአግባብ የታሠሩ የተቃዋሚ መሪዎች፣ ተማሪዎችና ጋዜጠኞች በአስቸኳይ ተፈትተው የእርምት እርምጃ እርምጃ እንዲወሰድ፣ የሚሉና ሌሎችም እንደሚገኙበት በፅሁፋቸው ላይ ተገልጿል፡፡

መሪዎቹ ለዩናይትድ ስቴትስ መንግሥትና ለዓለምአቀፉ ማኅበረሰብም ባቀረቡት ባለ ሦስት ነጥብ ሃሣብ የኢትዮጵያ መንግሥት ጅምላ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣዎችን መፈፀሙንና ሌሎችን ከፖለቲካና ከኢኮኖሚ ተሣትፎ ማግለሉን እስከቀጠለ አስፈላጊ የሆኑ የምጣኔ ኃብትና ወታደራዊ ማዕቀቦችን እንዲጥሉበት የሚልና ሌሎችም ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡

ከፓስተር ዶ/ር ገመቹ ኦላና ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ለመስማት ከላይ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የኦሮሞ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያን ኅብረትን ደብዳቤ ሙሉ ቃል ለማንበብ ከዚህ በታች የተያያዘውን ማገናኛ ይጫኑና ይከተሉ፡፡ http://www.uoec.org/site/wp-content/uploads/2016/01/UOEC_Statement-_on-Ethiopian-governmet_action_against_Oromo_students.pdf

XS
SM
MD
LG