ሂሮሽማ —
የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ጋር ሆነው ወደ ሂሮሽማ መታሰብያ የሰላም መናፈሻ ገብተው በመዘወወር ታሪክ ሰርተዋል።
ሂሮሺማ እ.አ.አ በ. 1945 ዓ.ም ሁለተኛው የአለም ጦርነት በተካሄበት ወቅት ነሀሴ ስድስት ቀን ላይ በአሜሪካ በአቶሚክ ቦብም የወደመች ከተማ ናት።
ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ የሂሮሽማ መታሰብያ የሰላም መናፈሻ በመጎብኘት ታሪክ ሰርተዋል
Previous slide
Next slide
የአሜሪካ ተዋጊ አይሮፕላኖች ሂሮሺማ ከተማ ላይ የጣሉት አቶሚክ ቦምብ ጥቅም ላይ ሲወል ከአለም የመጀመርያው ሲሆን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰውችን ፈጅቷል። ትውልዶች በአቶሚክ ቦምቡ መርዛማ ጨረራ ተጎጂ ሆነዋል።
የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ Cindy Saine ከቦታው የላከችውን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ ታቀርበዋለች።