ዋሽንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ፣ በ2 የስያ አገሮች የአንድ ሳምንት ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ቅዳሜ ከዋሽንግተን ይነሳሉ፤ በዓለም የመጀመሪያዋ የኑክሊየር ጥቃት ሰለባ በሆነችው የጃፓኗ ሂሮሽማም ቆይታ ያደርጋሉ።
የፕሬዚደንቱን ጉብኝት፣ "ዩናይትድ ስቴትስ ከእስያና ከፓሲፊክ አገሮች ጋር ለጀመረችው ግንኙነት፣ ሚዛን አስተካካይ ነው" ብሎታል ዋይት ኃውስ ባወጣው መግለጫ።
ዋይት ኃውስ አክሎም፣ "ዩናይትድ ስቴትስ ከክልሉ ሕዝብና መንግሥታት ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሚያጠናክርም ይሆናል" ብሏል።
ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በመጪው ዐርብ በጃፓኗ ኢሰ ሺማ በሚካሄደውና ለእርሳቸው የመጨረሻ የሆነውን የG-7 ጉባዔ ተካፍለው፣ በታሪካዊው የሂሮሽማ ጉብኝት፣ ጉዟቸውን ያጠቃልላሉ።