በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለጤና ዋስትና ከሰራተኞች ደሞዝ ላይ ከፊታችን ጥር ጀምሮ መቆረጥ እንደሚጀምር ተገለጸ


በመደበኛ ሥራ ላይ የተሠማሩ ዜጎች የጤና ዋስትና እንዲኖራቸው የሚያስገድደው ዓዋጅ ከፊታችን ጥር ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል።

የጤና መድን ዋስትና ድንጋጌው በመደበኛም ሆነ መደበኛ ባልሆኑ የምጣኔ ኃብት ዘርፎች ላይ የተሠማሩ ኢትዮጵያዊያን እንደኪሣቸው ሳይሆን እንደችግራቸው የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ ለሚደረግ የተሠራ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በተለይ በመደበኛ ሥራ ላይ የተሠማሩ ዜጎች የጤና ዋስትና እንዲኖራቸው የሚያስገድደው ዓዋጅ ከፊታችን ጥር ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል።

ከሠራተኞች ደሞዝ ላይ ለመድን ዋስትና የሚሆን ክፍያ መቆረጥ እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

ከቪኦኤ ጋራ ቃለ-ምልልስ ያደረጉት የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር ከሰተብርሃን አድማሱና በአሜሪካ ዓለማቀፍ የልማት ድርጅት (USAID) የጤና ሥርዓት ማጠናከሪያ ቡድን መሪ አቶ እሸቴ ይልማ በዚህ ዕቅድ ላይ ማብራሪያዎች ሰጥተዋል።

እስክንድር ፍሬው ተከታዩን ዘገባ አዘጋጅቷል ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

ለጤና ዋስትና የሚሆን ክፍያ ከሰራተኞች ደሞዝ ላይ ጥር መቆረጥ እንደሚጀምር ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:45 0:00

XS
SM
MD
LG