በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓለም “በ15 ዓመት ከቲቢ ትላለቀቃለች” - ዳብልዩ ኤች ኦ


የዓለም የጤና ድርጅት ወይም ዳብልዩ ኤች ኦ(WHO)
የዓለም የጤና ድርጅት ወይም ዳብልዩ ኤች ኦ(WHO)

ዓለም በመጭዎቹ 15 ዓመታት ውስጥ ቲቢን ለመፈፀም የሚያስችል ዕቅድ ይዟል፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት በወዲያኛው ሣምንት ውስጥ አዲስ አበባ ላይ በጠራው ዓለምአቀፍ ጉባዔ በዘላቂ ልማት ግቦች የታቀፈውን ቲቢን የመፈፀም ዒላማ ለመምታት ማኅበረሰቦችንና እስከአሁን በፀረ-ቲቢ ዘመቻ ላይ ያልተሣተፉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ማሣተፍ በሚቻልበት ሁኔታላይ መክሯል፡፡

ቲቢን ለማቆም የተደረገው ዘመቻ በያዝነው ዓመት የተጠናቀቀው የሚሌኒየሙ የልማት ግቦች አካል የነበረ መሆኑን በዓለም የጤና ድርጅት የኤችአይቪና የቲቢ ማኅበረሰባዊ ተሣትፎ መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ኃይለየሱስ ጌታሁን ለቪኦኤ የገለፁ ሲሆን ቲቢን ወደማጥፋት የሚወስደው ቀጣዩ እርምጃ ለሚቀጥሉት 15 ዓመታት የሚካሄደው ቲቢን የመፈፀም እንቅስቃሴ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በዚህም መሠረት በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር በ2023-24 ዓ.ም በቲቢ አምጭው ሕዋስ እንደአዲስ የሚያዘው ሰው ቁጥር በሰማንያ ከመቶ፤ በቲቢ ምክንያት የሚሞተው ሰው ቁጥር ደግሞ በዘጠና ከመቶ እንደሚቀንስና ቲቢ የማኅበረሰብ ጤና ሥጋት መሆኑ እንደሚያበቃ ዶ/ር ኃይለየሱስ ተናግረዋል፡፡

እዚህ ግብ ላይ ለመድረስ በርካታ መድኃኒቶችን መቋቋም የሚችለውን ሌሎችም የቲቢ ዓይነቶችን በተሣካ ሁኔታ ለማከም የሚያስችሉ ፍቱን መድኃኒቶችና ቴክኖሎጂ፣ ክትባትና ገንዘብ አስፈላጊ መሆናቸውን ዶ/ር ኃይለየሱስ ጠቁመው “ዓለም እስከአሁን የተጨበጡ ስኬቶችን አጠንክሮ ወደፊት ከተራመደ የዘላቂው ልማት ግቦች ሊደረስባቸው የሚችሉ ናቸው” ብለዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ዓለም "በ15 ዓመት ከቲቢ ትላለቀቃለች" - ዳብልዩ ኤች ኦ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:26 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG