በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኮንሶ እንደራሴ እንዲመለሱ ተጠየቀ


የኮንሶ ገበሬዎች ዘር እየዘሩ [የአሶሽየትድ ፕረስ ፎቶ/AP]
የኮንሶ ገበሬዎች ዘር እየዘሩ [የአሶሽየትድ ፕረስ ፎቶ/AP]

ለፌደራሉ መንግሥት አቤቱታውን እንድናቀርብ የኮንሶ ሕዝብ ወክሎ ልኮናል ያሉ ሰዎች አዲስ አበባ ይገኛሉ፡፡

ለፌደራሉ መንግሥት አቤቱታውን እንድናቀርብ የኮንሶ ሕዝብ ወክሎ ልኮናል ያሉ ሰዎች አዲስ አበባ ይገኛሉ፡፡

ለፌደራሉ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትና መሥሪያ ቤቶች የቀረቡት ጥያቄዎች ለተወካዮች ምክር ቤት ከወረዳው የተመረጡት እንደራሴ የሕዝብ እምነት በማጣታቸው ምክንያት እንዲመለሱ፣ የኮንሶ ወረዳ እራሱን ችሎ በዞን ደረጃ እንዲዋቀር ጥያቄ ከቀረበበት ጊዜ አንስቶ በሕዝቡ ላይ እየደረሰ ነው ያሉት ጥቃትና እንግልት እንዲቆም እንዲደረግ እና የዞንነት ጥያቄው እንዲታይለት የሚሉ ናቸው፡፡

የሕዝቡ ተወካዮች ነን የሚሉት ሰዎች የሃምሣ ሺህ ሰው ፊርማ መሰብሰባቸውን አመልክተው እንደራሴው የሕዝቡን እምነት ያጡት ጥያቄውን በማጣጣላቸውና ሕዝቡን በመዝለፋቸው ነው ብለዋል፡፡

“ተወካዮቹ” ጥያቄዎቻቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለፌደራል የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሺንና እምባ ጠባቂ ተቋም፣ ለፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴርና ሌሎችም ባለሥልጣናትና በጠቅላላው ለዘጠኝ መሥሪያ ቤቶች ማስገባታቸውን ገልፀዋል፡፡

በሕዝቡ ላይ ይደርሣል ያሉትን ጥቃትና እንግልት የሚመረምር ቡድን ወደ ኮንሶ እንደሚላክ ከከፍተኛ ባለሥልጣናቱ የተነገራቸው መሆኑን ከተወካዮቹ አንዱ ለቪኦኤ በሰጡት ቃለምልልስ አመልክተዋል፡፡

ለተጨማሪ ከተወካዮቹ አንዱ የሆኑትን የአቶ አቤል ለሜቻንና የመለስካቸው አምሃን ቃለ-ምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

የኮንሶ እንደራሴ እንዲመለሱ ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:30 0:00

XS
SM
MD
LG