በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በካምቦድያ ተከታታይ ስብሰባ አካሄደዋል

ካምቦድያ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የሚኖራትን የግንኙነት መሰረት ፍጻሜ ላይ ለማድረስ በሰብአዊ መብት፣ በአጠቃላይ ነጻነትና በመልካም አስተዳደር ረገድ ማሻሽል የማሳየትዋ ጉዳይ ወሳኝ እንደሚሆን ጆን ኬሪ አስገንዝበዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ዛሬ ካምቦድያ ውስጥ ከባለስልጣኖች ጋር ተከታታይ ስብሰባ ባካሄዱበት ወቅት ዋናዎቹ የንግግር ነጥቦች በሰብአዊ መብት ላይ ያላቸው ስጋትና የጋራ ንግድ ጉዳይ እንደነበር ታውቋል።

ካምቦድያ ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የሚኖራትን የግንኙነት መሰረት ፍጻሜ ላይ ለማድረስ በሰብአዊ መብት፣ በአጠቃላይ ነጻነትና በመልካም አስተዳደር ረገድ ማሻሽል የማሳየትዋ ጉዳይ ወሳኝ እንደሚሆን ጆን ኬሪ አስገንዝበዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የካምቦድያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሁን ሰን (Hun Sen) እና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ከም ሶካ (Kem Sokha) ከሚገኙባቸው ባለስልጣኖች ጋር በተናጠል ተገናኝተው ከተነጋገሩ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ነው ይህ ያሉት።

XS
SM
MD
LG