በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጆን ኬሪ በእሥረኤል ጉብኝታቸው የሽብር ተግባር "ትርጉም-የለሽ" ነው ብለዋል


ኬሪ ሽብርተኘትን ጨርሶ ለማስወገድ በሚችበት ሁኔታ ላይ ከናታንኛሁ ጋር እንደሚወያዩ ተገልጿል።

በቅርቡ ኢየሩሳሌም ውስጥ የደረሰውን የፍልስጥኤማውያን ጥቃት፣ "ሽብርተናነት" ሲሉ፣ ዛሬ ማስከኞ ከእሥራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንዣሚን ናታንኛሁ ጋር የተገናኙት የዩናይትድ ስቴትስ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ መፈረጃቸው ተሰማ።

ኬሪ፣ ሽብርተኘትን ጨርሶ ለማስወገድ በሚችበት ሁኔታ ላይም፣ ከናታንኛሁ ጋር እንደሚወያዩ ተገልጧል።

ኬሪ በእሥረኤል ጉብኝታቸው ወቅት፣ ይህ ዓይነቱ የሽብር ተግባር "ትርጉም-የለሽ" መሆኑንም፣ ከናታንኛሁ ጋር በሚወያዩበት ወቅት እንደሚያሰምሩበት ተገልጧል።

ናታንኛሁ በበኩላቸው፣ እሥራኤል በየሰዓቱ በእስላማሚ ነውጠኛነት ላይ ጽኑ ውጊያ እንደምታካሂድ አመልክተው፣ «ውጊያውም» አሉ፣ "በኋላ-ቀርነት ላይ የሚካሄድ የሥልጣኔ ጦርነት ነው" ብለዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

ጆን ኬሪ በእሥረኤል ጉብኝታቸው የሽብር ተግባር "ትርጉም-የለሽ" ነው ብለዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:55 0:00

XS
SM
MD
LG