በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካና ሩሲያ ለመስማማት እየተነጋገሩ ነው


ፋይል ፎቶ - [አሶሽየትድ ፕረስ/ AP]
ፋይል ፎቶ - [አሶሽየትድ ፕረስ/ AP]

አሜሪካና ሩሲያ አብረው ከሠሩ ሦሪያ ውስጥ ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃን ኬሪ አስታወቁ፡፡

አሜሪካና ሩሲያ አብረው ከሠሩ ሦሪያ ውስጥ ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃን ኬሪ አስታወቁ፡፡

ሩሲያ በሦሪያና በዩክሬን ጉዳዮች ላይ ልትጫወት ስለምትችላቸው ሚናዎቿ ኬሪ ዛሬ ሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ ውስጥ ከሃገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሁለቱ ሃገሮች ከሌሎች ኃያላን መንግሥታት ባለሥጣናት ጋር ከነገ በስተያ ዓርብ ኒው ዮርክ ላይ ከመገናኘታቸው በፊት ሦሪያን አስመልክቶ በመካከላቸው ያለውን ልዩነት አንጥረው ለማውጣት እየጣሩ ናቸው ተብሏል፡፡

ባለሥልጣናቱ ኒው ዮርክ ላይ በሚያደርጉት ስብሰባ የሦሪያን የሰላማዊ ሽግግር ሂደት አስመልክቶ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚያወጣውን የውሣኔ ረቂት ያፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

አሜሪካና ሩሲያ ለመስማማት እየተነጋገሩ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:15 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG