በአፍሪቃ የደህንነት አደጋ የደቀነውን ዓለም አቀፍ ሽብር ጉዳይ ያጤኑ የምክር ቤት አባላት በአገሮቹ ያለውን የሰብዓዊመብት አያያዝና መሪዎች በአስተዳደር ስልጣናቸው ከለላ የሚፈጽሟቸውን ጥሰቶች፤ “እንዳታይ” ወይም
“እንድታልፍ አድርጓታል፤” ሲሉ፤ ስጋታቸውን ገለጡ።
በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የአፍሪቃ ጉዳዮች ረዳት ሚንስትር Linda Thomas-Greenfield ለምክር ቤቱየውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ በበኩላቸው ከትላንት በስቲያ በሰጡት የምስክርነት ቃል፥ አገሮቹ “አለባቸው” ስላሉት “እጅግ አሳሳቢተጋላጭነት” እና እንዲሁም “አፋጣኝ ትኩረት ይሻል” ስላሉት “የአቅም ክፍተት” አብራርተዋል።
መስመር አስምረን፥ በሰብአዊ መብት አያያዛችሁ ሳቢያ በጸረ-ሽብር ዘመቻው ከእናንተ ጋር አብረን አንሠራም አንላቸውም።ነገር ግን የሰብአዊ መብቶችንና የሲቪል መብት ነጻነቶችን እንዲያከብሩ ግን ግፊት ለማድረግ እንጠቀምበታለን።የአፍሪቃ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚንስትር Linda Thomas-Greenfield
አሸባሪ ቡድኖች በቀጥታ ገንዘብ በመስጠት ተዋጊዎችን እንደሚመለምሉ ያስረዱት የአፍሪቃ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይሚንስትሯ “ያን ለመቋቋም መንግስታቱ በምትኩ “የትምሕርትና የሞያ ክህሎት ስልጠና ዕድሎችን ለመፍጠር ያላቸውንአቅርቦትና አቅም በሙሉ መጠቀም አለባቸው፤” ብለዋል። ዋናውም የዩናይትድ ስቴትስ ትኩረት የተባሉትን እድሎች በእነኚህአገሮቹ ውስጥ ለመፍጠር የተያዘውን ጥረት ለታለመለት ዓላማ ማብቃቱ ላይ ነው።
በዚህም ሳቢያ ዩናይትድ ስቴትስ መንግስታቱ በዓለም አቀፉ የጸረ-ሽብር ዘመቻ ሁነኛ አጋር እስከሆኑ ድረስ በሰብዓዊ መብትከበሬታ ላይ ለሚሰነዘሩት ጥቃቶችና ለሚታዩት የአስተዳደር ብልሹነቶች ይለፍ እየሰጠች ነው፤ ሲሉ በዩናይትድ ስቴትስ ምክርቤት የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ከፍተኛ አመራር አባል ሴናተር Ben Cardin ስጋታቸውን ገልጠዋል።