ዋሽንግተን ዲሲ —
ጎንደር ከተማ ውስጥ በመገበያያ ቦታነት ረጅም ጊዜ እንዳስቆጠረ የሚነገርለትና በተለምዶ “ቅዳሜ ገበያ” ተብሎ የሚጠራው የገበያ ቦታ ትናንት ምሽት በደረሰ የእሳት አደጋ ወደ 420 ሱቆች ሙሉ ለሙሉ መውደማቸው ተገለጸ።
የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ሱቅ የተቃጠለባቸው ነጋዴዎች ሆን ተብሎ የተደረገ ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬ እንዳላቸው ገልጸው እሳቱን ተቆጣጥሮ ንብረቱን ከውድመት ማትረፍ ያልተቻልው በመንግሥት ታጣቂዎች ተኩስ ምክንያት ነው ይላሉ።
የክልሉ መንግስት ቃል አቀባይ በበኩላቸው እሳቱ በምን እንደተነሳ እንዳልታወቀ ግልጸው ሕዝብና መንግስት ባደረገው ርብርብ እሳቱ ሊጠፋ ችሏል ብለዋል።
ጽዮን ግርማ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው የደምጽ ፋይል ያድምጡ።