በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ክልል የተፈጠረው ውጥረት ቀጥሏል


የአማራ ክልል ካርታ - ከተመድ የተገኘ

በአማራ ክልል የተፈጠረው ውጥረት ትናንት እና ዛሬ መባባሱን እና በመተማ የሰው ሕይወት መጥፋቱን በርካታ ንብረት መውደሙን በደብረ-ታቦር ማረምያ ቤት መቃጠሉን በአምቦጊዮርጊስ እንዲሁ የሰው ሕይወት መጥፋቱ በአጠቃላይ በክልሉ አብዛኞቹ ከተሞች የመከላከያ ሰራዊት መግባቱና የተኩስ ድምፅ ያለማቋረጥ መሰማቱን የፓርቲው ተወካዮችና ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉ ነዋሪዎች ገለጹ።

የክልሉ መንግሥት ቃል-አቀባይ ሁኔታውን ለማረጋጋት እየሠራ መሆኑንና የተደራጀ መረጃ በነገው ዕለት እንደሚሰጥ ገልጿል።

በዚህ ጉዳይ ላይ የተጠናከረውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG