በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጎንደር ላይ የሃያ አራት ዓመት ወጣት ተገደለ

በዛሬ ዕለት ጎንደር
በዛሬ ዕለት ጎንደር

ጎንደር ከተማ ውስጥ አንድ የሃያ አራት ዓመት ወጣት ዛሬ በፀጥታ ኃይሎች መገደሉን ቤተሰቦቹ ገለጹ። የተገደለበት ምክንያትም “ነጭ ቲ-ሸርት በመልበሱ ነው” ብለዋል። የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ ግን የወጣቱን መገደል አረጋግጠው የተገደለው ግን “በልብሱ ምክንያት አይደለም” ብለዋል፡፡

ጎንደር ከተማ ውስጥ አንድ የሃያ አራት ዓመት ወጣት ዛሬ በፀጥታ ኃይሎች መገደሉን ቤተሰቦቹ ገለጹ። የተገደለበት ምክንያትም “ነጭ ቲ-ሸርት በመልበሱ ነው” ብለዋል። የክልሉ መንግሥት ቃል አቀባይ ግን የወጣቱን መገደል አረጋግጠው የተገደለው ግን “በልብሱ ምክንያት አይደለም” ብለዋል፡፡

የሃያ አራት ዓመቱ ወጣት ግዛቸው ከተማ የተገደለው ሞተር ቢስክሌት እያሽከረከረ ሳለ መሆኑን የሚናገሩ አሉ፡፡

ለቪኦኤ መግለጫ የሰጡት ከሟች ግዛቸው ዘመዶች አንዱ ወጣቱ ከተመታ በኋላ የፀጥታ አባላቱ በኮድ አንድ ተሽከርካሪ ይዘውት ሲሄዱ በሕይወት እንደነበረና እነርሱ ግን አስከሬኑን መረከባቸውን ተናግረዋል፡፡

ወጣቱ የተገደለበት ሁኔታ ወደፊት እንደሚጣራ የጠቆሙት የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊው አቶ ንጉሡ ጥላሁን “የከተማውንና የክልሉን ሰላም ለማወክ ጎን ለጎን መልዕክት ይዘው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች አሉ” ብለዋል፡፡

ጽዮን ግርማ ማምሻውን ወደ ጎንደር ደውላ ተከታዩን አጠራቅራለች።

ለተጨማሪ የተያያዘውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

ጎንደር ላይ የሃያ አራት ዓመት ወጣት ተገደለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:43 0:00

XS
SM
MD
LG