በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ የአራተኛና የመጨረሻ የኑክሌር ጥበቃ የመሪዎች ጉባዔ በዋሽንግተን እያስተናገዱ ነው


የመሪዎቹ ጉባዔ ዓብይ አላማ፥ አሸባሪዎች የኑክሌር ጦር መሣሪያ እጃቸው እንዳይገባና መጠቀም እንዳይችሉ መከላከል ነው ሲሉ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ አስረድተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ የዚህ ዓመቱን አራተኛና የመጨረሻ የኑክሌር ጥበቃ የመሪዎች ጉባዔ በዋሽንግተን ያስተናግዳሉ።

ዛሬና ነገ ለሁለት ቀናት በሚደረገው ስብሰባ ላይ የሚሳተፉት ከ 50 በላይ መሪዎች፥ ለኑክሌር ግንባታ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን በተሻለ ዘዴ መጠበቅ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ይወያያሉ።

ፕሬዘዳንት ኦባማ በጉባዔው ዋዜማ በዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ላይ ባቀረቡት አስተያየት፥ ዛሬ ለዓለማችን ፀጥታና ሰላም አደገኛው ስጋት የኑክሌር ሥርጭትና ምናልባትም የኑክሌር ጦር መሣሪያዎችን መጠቀም ነው ብለዋል።

ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ የአራተኛና የመጨረሻ የኑክሌር ጥበቃ የመሪዎች ጉባዔ በዋሽንግተን እያስተናገዱ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:18 0:00

የመሪዎቹ ጉባዔ ዓብይ አላማም፥ አሸባሪዎች የኑክሌር ጦር መሣሪያ እጃቸው እንዳይገባና መጠቀም እንዳይችሉ መከላከል ነው ሲሉ አስረድተዋል።

ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዩ ቪክተር ቢቲ ዘግቦበታል። ሰሎሞን ክፍሌ አቅርቦታል።

ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ የአራተኛና የመጨረሻ የኑክሌር ጥበቃ የመሪዎች ጉባዔ በዋሽንግተን እያስተናገዱ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:56 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG