በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኒኩሌር፣ ስጋቱና አስፈላጊነቱ ለኢትዮጵያ


ኢትዮጵያ በመጭዎቹ ከአሥር እስከ ሃያ ዓመታት የኒኩሌር ኃይል ባለቤት ልትሆን ትችላለች፣ መሆንም አለባት ብለው አንድ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁር ያምናሉ፡፡

በጃፓን ፉኩሺማ ዳይቺ የኒኩሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ የደረሰው ርዕደ-ምድርና ፁናሚ ወለድ አደጋ በአካባቢው ላይ ከፍ ያለ ሥጋት አሣድሮ ሰንብቷል፡፡ ሁኔታው ከአካባቢው ሃገሮች የዘለቀም ችግር ሊፈጥር እንደሚችል የፈሩ በጃፓን ምርቶች ላይ ዕገዳ እስከመጣልም የደረሱ ሃገሮች አሉ፡፡

ለመሆኑ ይህ የኒኩሌር ሥጋት ምንድነው? ምሥራቅ አፍሪካና ኢትዮጵያ ዘንድ የሚደርስ ሁኔታ ይኖራል? የሚያስከትለውስ ጉዳት እንዴት ሊመጣና ምን ሊሆን ይችላል? ኢትዮጵያ የኒኩሌር ኃይል ባለቤት ልትሆን የምትችልበት ሁኔታ አለ? ያስፈልጋታል? ከሆነችስ እንዴትና መቼ?

የተፈጥሮ አካባቢ፣ ሣይንስና ሕይወት ፕሮግራም አዘጋጅ ሰሎሞን አባተ ወደአዲስ አበባ ደውሎ ነበር፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሣይንስ ኮሌጅ በፊዚክስ ዲፓርትመንት ረዳት ፕሮፌሰር፣ በድኅረ ምረቃና በቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የኒኩሌር ፊዚክስና የኒኩሌር ሬድዬሽን ፊዚክስ መምህር የሆኑትን ዶክተር ጥላሁን ተስፋዬን አነጋግሯል፡፡

የውይይታቸውን የመጀመሪያና ሁለተኛ ክፍሎች ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG