በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜን ኰሪያ የሃይድሮጅን ቦምብ ሙከራ ማድረጓን አስታወቀች


ሰሜን ኰሪያ የሃይድሮጅን ቦምብ ሙከራ የሚያሳይ (ፎቶ አሶሽየትድ ፕረስ/AP Photo)
ሰሜን ኰሪያ የሃይድሮጅን ቦምብ ሙከራ የሚያሳይ (ፎቶ አሶሽየትድ ፕረስ/AP Photo)

ሰሜን ኰሪያ ያደረገችውን የሃይድሮጅን ቦምብ ሙከራ ዩናይትድ ስቴትስም ሆነች ሌሎች ምዕራባውያን ውድቅ አድርገው ድርጊቱን አውግዘዋል።

ሰሜን ኰሪያ አጥጋቢ የሃይድሮጅን ቦምብ ሙከራ ማድረጓን ዛሬ ረቡዕ አስታወቀች፣ ከዓለም ኃያላን መንግታትም ከፍተኛ ነቀፋን አስከተለባት።

"ሙከራው እራስን ከመከላከል አኳያ የተካሄደ ነው" ሲል መልስ የሰጠው መንግታዊው የሰሜን ኰሪያ መገናኛ አውታር፣ ከዚህ አኳያ "ትንኮሳና ነገር ፍለጋ" ያለውን ዩናይትድ ስቴትስ የተለያዩ ሙከራዎች ጠቅሷል።

ዳሩ ግን ዩናይትድ ስቴትስም ሆነች ሌሎች ምዕራባውያን፣ የሰሜን ኰሪያውን ማስተባበያ ውድቅ አድርገው ድርጊቱን አውግዘዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በበኩሉ ጉዳዩን በቅርብ እየተከታተለ መሆኑን ያወጣውን መግለጫ ከዚህ በታች ካለው የትዊተር ፋይል ያገኙታል።

በተጨማሪም የዜና ዘገባ አለን የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያዳምጡ።

ሰሜን ኰሪያ የሃይድሮጅን ቦምብ ሙከራ ማድረጓን አስታወቀች
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:42 0:00

XS
SM
MD
LG