በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ግዙፉ የአፕል ኩባንያ የአሸባሪዎች ጥቃት ምርመራ ላይ ትብብር እንዲያደርግ ተጠየቀ


የዩናትድ ስቴትስ የጠቅላይ ፍርድቤት ግዙፉን የአፕል ኩባንያ በሳንበርዲኖ ለደረሰው የአሸባሪዎች ጥቃት ምርመራ ትብብር እንዲያደርግ ጠየቀ።

የአፕል ኩባንያ የአሽባሪዎቹን የስልክ ምልልስ ባለው የቴክኖሎጂ ብቃት በማውጣት የዩናተድ ስቴትስ መንግሥስት የወንጀል ምርመራ አካል ኤፍቢአይ (FBI) በሚያደርገው ምርምራ ላይ እንዲተባበር የጠቅላይ አቃቤ ሕግ ባቀረበው ጥያቄ ዙሪያ በኮንግረስ ፊት በትላንትናው ዕለት በየበኩላቸው ጉዳያቸውን አስረድተዋል።

የዩናይትድ ስቴትሱ የወንጀል ምርመራ የአሸባሪውን ሰይድ ሪዝዋን ፋሩክ በአይፎን ያደረገውን የስልክ ምልልስ ለመስማት የአፕል አዲስ ቴክኖሎጂን መጠቀም እንደሚፈልግም በግልፅ አስታውቋል። ባሳለፍነው የታኅሳስ ወር በካሊፎርኒያ ሳንበርዲኖ አሸባሪው ፋሩክ እና ባለቤቱ 14 ሰዎችን እንደገደሉና 22ሰዎች እንዳቆሰሉ ይታወሳል።

የኤፍቢአይ (FBI)ዋና መርማሪ ጄምስ ኮሜይ (James Comey) ለዩናይትድ ስቴትሱ ምክርቤት የሕግ ጉዳይ አስፈፃሚ ኮሚቴ እንደገለጹት፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሌሎች ወንጀሎችንም ለመከላከል ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል።

የካሊፎርኒያው ከፍተኛ ፍርድ ቤት አፕልን ይህን ቲክኖሎጂውን ለወንጀል ምርመራ ይጠቅም ዘንድ እንዲፈቅድ ሕግ ካወጣ ለተለያዩ ወንጀሎች ምርመራ ከፍተኛ አስተዋፆ ይኖረዋል።

ጄምስ ኮሜይ "በሳን በርናንዲኖ የተከሰተው ይኸው ነው። የስልክ ምልልሱ መረጃ ቢገኝ ነገሮችን ያቀለዋል። የሕግ አውጪው አዲሱን ሕግ ቢያፀድቅ የተሻለ ነው። በወንጀል ምርመራ ጉዞ ውስጥ ጠቃሚ መረጃዎችን ማግኘት እንዲቻልና ምርመራው በአጥጋቢ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ይረዳል።" ብለዋል።

የኤፍቢአይ (FBI) ዳይሬክተር ጄምስ ኮሜይ
የኤፍቢአይ (FBI) ዳይሬክተር ጄምስ ኮሜይ

​በሌላ ወገን ደግሞ የአፕል ኩባንያ አይፎን (iphone) በሚጠቀሙ ደምበኞቻችን እምነትን እናጣለን ሲሉ የድርጅቱ ጠበቃ ብሩስ ስዌል ተከራክረዋል። "የተጠየቅነው ቴክኖሎጂ በሁሉም አይፎን ላይ አሁን እየተጠቀምንበት ያለውን ቴክኖሎጂ ነው። በጣም ሰፊና ተመሳሳይ ነው። አንድን መስመር ብቻ ነጥሎ የሚከፍት አይደለም።"

የFBI ጥያቄን ተግባራዊ ማድረጉ ከፍተኛ የመረጃ ቀውስ ሊያመጣ ይችላል ይላል የሳይበር ሴኩሪቲው ማርክ ሮተንበርግ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጠው ቃል፤

"ሕጉ አንዴ ከወጣና ቴኖሎጂውን መጠቀም ከጀመርን ለዩናይትድ ስቴትስ መንግስት እንደታሰበው ቀላል አይሆንም። ምክንያቱም ሌሎች ሃገሮችም ይህንን ቴክኖሎጂ ለመጠቀም የሚያግዳቸው ነገር አይኖርም። እንደ ቻይና እና ሩስያ ያሉ ሃገሮችንም ማለቴ ነው። በጣም ከባድ ምርመራ የሚጠይቁ ወንጀሎች ስላሉ ነው ይህን ቴክኖሎጂ ለመጠቅም የተፈለገው። ከዛ ባለፈ ግን ወደ ያልተፈለገ ውስብስብ ዓለምአቀፍ አጣብቂኝ ውስጥ ልንገባ እንደምንችል ቀድመን መረዳት ያስፈልገናል።"

የሕግ አውጪዎቹ በሌላ በኩል ደኅንነትና የግል ጉዳይን በእኩል የምናከብረው ጉዳይ ይሆናል ብለዋል። የዴሞክራት ፓርቲ አባል የሆኑት ጄሪ ናድለርም አስተያየታቸውን እንዲህ በማለት ገልጸዋል። "ጥንቃቄ በተሞላበት የግል ጉዳዮችንና የአፕል ቴክኖሎጂ በተቃዋሚዎቹ መታመኑ እንዲቀጥል ተጨማሪ ሕግ ይኖራል። በወንጀለኞችና በሰላማዊ ሰዎች መካከል ያለውን የመለየቱ ሥራ ግን ጥንቃቄ ሊወሰድበት የሚገባ ነው።"

ፍርድቤቱ አዲሱን ሕግ እስከሚያፀድቅ የአፕል መስሪያ ቤትና ኤፍቢአይ (FBI) ፍጥጫቸውን ወደ ፍርድቤት ያዞራሉ።

ግዙፉ የአፕል ኩባንያ የአሽባሪዎች ጥቃት ምርመራ ላይ ትብብር እንዲያደርግ ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:58 0:00

XS
SM
MD
LG