በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦባማ ፀረ-ሽብር ሥልታቸውን ይፋ አደረጉ


ዩናይትድ ስቴትስ ሽብር ፈጠራን ለመዋጋት የምታደርገውን ጥረት በድጋሚ ያረጋገጡት ፕሬዚዳንቷ ባራክ ኦባማ አሜሪካዊያን ለፍርሃት እንዳይንበረከኩ ጥሪ አሰምተዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ትናንት ምሽት ላይ ለሕዝባቸው በቴሌቪዥን በቀጥታ ባደረጉት ንግግር የሃገሪቱን ደኅንነት አስጠብቅባቸዋለሁ ያሏቸውን ሥልቶች በዝርዝር ተናግረዋል፡፡

የካሊፎርኒያዪቱ ሳን በርናርዲኖ ውስጥ በአሜሪካዊው ሰዒድ ፋሩቅ እና የፓኪስታን ተወላጅ በሆነችው ሚስቱ ታሽፊን ማሊክ የተፈፀመውን ጅምላ ግድያ “በእሥላማዊ መንግሥት ቡድን የተነነሣሣ የሽብር አድራጎት ነው” ብለው መርማሪዎች እንደሚያምኑ እየተነገረ ነው፡፡

ፕሬዚዳንት ኦባማ በትናንት ምሽት ንግግራቸው ግድያውን ያነሣሣው ምን እንደሆነ ሲናገሩ “ሁለቱ ሰዎች በአሜሪካና በምዕራቡ ዓለም ላይ ጦርነት እንዲከፈት ወደሚጣራ የተዛባ የእሥልምና ትርጉምን ወዳነገበ የተጋነነ መነሣሣት ወደመራው የጭለማ መንገድ ተጉዘዋል፤ ማጥቂያ መሣሪያዎችን፣ ጥይትና ፈንጂዎችን አከማችተዋል፤ ስለዚህ ይህ የሽብር አድራጎት ነው” ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ የሳን በርናርዲኖው ጥቃት በአንድ ኃይል የታዘዘ ይሁን ወይም የአንዳች ግዝፈት ያለው ሴራ አካል ቆርጦ ለመናገር የሚያስችል ማስረጃ መርማሪዎቹ እስከአሁን አለማግኘታቸውን ፕሬዚዳንቱ አመልክተዋል፡፡

“አሜሪካ በሽብር ፈጣሪዎች ላይ ጫናዋን እያበረታች በመጣች መጠን ሥጋቶቹም ገፅታቸውን እየቀያየሩ እየመጡ ናቸው” ብለዋል፡፡

“በመስከረም 1994 ዓ.ም የተፈፀመብንን የመሰለን ጥቃት ለመመከት ያለን ብቃት ይበልጥ እየተወሳሰበ በመጣ መጠን ሽብርተኞቹ ለመፈፀም ቀለል ወዳሉ፤ በእኛ ማኅበረሰቦች ውስጥ ወደተለመዱት ዓይነት መደዳ ግድያዎች እያዘነበው ነው” ብለዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡

ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ የአሜሪካውያንን ደህንነት በተሻለ ለመጠበቅ ያሰሙት ንግግር
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:09 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ዩናይትድ ስቴትስ ኢራቅና ሦሪያ ውስጥ በእሥላማዊ መንግሥት ቡድን ላይ ጫና ማሣደሯን እንደምትቀጥል ቃል የገቡት ፕሬዚዳንት ኦባማ ፅንፈኞቹን ድል ለመንሣት በዩናይትድ ስቴትስ የሚመራውን ጥምረት ይበልጥ እየገነቡና እያጠናከሩ እንደሚቀጥሉ፤ ለሦሪያ ቀውስም የፖለቲካ መፍትኄ ለመፈለግ እንደሚጥሩ ተናግረዋል፡፡

ትዳር ከመመሥረት ጋር የተያያዘው የቪዛ መርኃ ግብር እንደገና እንዲፈተሽ ጠይቀዋል ፕሬዚዳንት ኦባማ፡፡

እስከአሁን በአይሲል ላይ እየተካሄዱ ያሉ ድብደባዎችን የአሜሪካው ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ በራሣቸው ሥልጣን እያዘዙ መቆየታቸውን የተናገሩት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በሽብር ፈጣሪዎች ላይ በሚካሄደው ዘመቻ ወታደራዊ ኃይል ማንቀሳቀስ እንዲችሉ የተወካዮች ምክር ቤቱ ይሁንታ እንዲሰጣቸው በድጋሚ ጠይቀዋል፡፡

እንደ ሳን በናርዲኖው ዓይነት ሌላ ጥቃት እንዳይፈፀም ኦባማ ስልቶቻቸውን በተከታታይ እየፈተሹ እንደሚለዋውጡና የአሜሪካን ሕዝብ ደኅንነት ለማረጋገጥ በሚያደርጉት ጥረት እንደሚገፉ ፕሬዚዳንቱ በዚሁ የትናንት ምሽት ንግግራቸው ቃል ገብተዋል፡፡

ዘገባውን ሰሎሞን አባተ አቅርቦታል ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኦባማ ፀረ-ሽብር ሥልታቸውን ይፋ አደረጉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:11 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG