በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስልኩን “ክፈተው”፤ “አልከፍትም” - የአሜሪካ መንግሥት ና የአፕል ውዝግብ


የአፕል ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቲም ኩክ የአሜሪካ መንግሥት ጥያቄና አቋም’ኮ “አስደንጋጭ ነው” ብለውታል።

በዩናይትድ ስቴትሷ ካሊፎርኒያ ግዛት ውስጥ በምትገኘው ሳን በርናርዲኖ ከተማ በቅርቡ በከፈቱት የሽብር ጥቃት 14 ሰው ከገደሉትና በተኩስ ልውውጥ ከተገደሉት ሁለት አጥቂዎች አንደኛው ይዞት የነበረው አይፎን ስልክ እንዲከፈትለት በሚፈልገው የዩናይትድ ስቴትስ ፌደራል ምርመራ ቢሮና አልከፍትም በሚለው በስልኩ አምራች አፕል ኩባንያ መካከል የተነሣው ውዝግብ አሁንም ተካርሮ እንደቀጠለ ነው።

ብዙ ቁጥር ያላቸው የመረጃ ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የአፕልን ሃሣብ እንደሚያደንቁ ቢናገሩም በዚህ በአሁኑ አጋጣሚ ግን አፕል በደረሰው የዳኛ ትዕዛዝ መሠረት ስልኩን መክፈት የሚቻልበትን መንገድ መፍጠር አለበት ይላሉ።

የአፕል ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቲም ኩክ የአሜሪካ መንግሥት ጥያቄና አቋም’ኮ “አስደንጋጭ ነው” ብለውታል።

“አፕል ለሽብርተኞች ፍቅር ወይም ኀዘኔታ የለውም” የሚሉት ኩክ ሳይድ ሪዛን ፋሩቅ ይዞት የነበረውን አይፎን ለመክፈት የሚያስችል ዘዴ መፍጠር ግን ይበጥል አደገኛ፤ ለአፕል ደንበኞች ደኅንነትም አስጊ እንደሚሆን እያስጠነቀቁ ነው።

የደንበኞቻችን ገንዘባቸው፤ የጤናቸው መረጃ፣ ያሉበት ቦታ፣ በስልኮቻቸው የያዟቸው መረጃዎች፣ የስልክ ንግግሮቻቸው፣ የግል ገመናቸው የመጠበቁ ነገር ሁሉ “አደጋ ላይ ይወድቃል” ብለዋል።

“የሚያመዛዝን ሕሊና ያለው አንድም ሰው እንዳህ ዓይነት ጥያቄ አያቀርብም” ብለዋል ቲም ኩክ።

ምንም እንኳ የቀድሞው የዳኛ ትዕዛዝ የወጣው ከሳንበርናርዲኖ አካባቢ የወረዳ ፍርድ ቤት ሲሆን ውዝግቡ እየተጠናከረና የአፕል እምቢተኝነት እየባሰ ሲሄድ ግን መንግሥቱ ጉዳዩን ዛሬ ፌደራል ችሎት ፊት ይዞ ቀርቧል።

ስለ ፕራይቨሲ ወይም የግል ገመና ምንነትና የመጠበቁ አስፈላጊነት ዝርዝር ማብራሪያ የሰጡት ከብሌን ኮርፕ ባለቤቶችና የሥራ ኃላፊዎች አንዱ የሆኑት አቶ ሚካኤል እንዳለ አፕል ቀደም ሲል የቀረበለትን ወደ ሁሉም ስልኮች መግባት የሚያስችል ዘዴ እንዲሠራ የሚጠይቅ ሃሣብ ውድቅ ማድረጉ የሚያስደንቀው እንደሆነ ጠቁመው የመጨረሻውን አንዷን ብቻ ስልክ እንዲከፍት የተላለፈውን የዳኛ ትዕዛዝ ማክበር አለበት ብለው እንደሚያስቡ ገልፀዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ስልኩን “ክፈተው”፤ “አልከፍትም” - የአሜሪካ መንግሥት ና የአፕል ውዝግብ
please wait

No media source currently available

0:00 0:21:13 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG