በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአርበኞች ግንቦት ሰባት መሪ ለአዉሮፓ ፓርላማ ንግግር አደረጉ


የአርበኞት ግንቦት ሰባት መሪ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ አሜሪካ በሚገኘው መኖርያቸው በልዊስበርግ (Lewisburg, Pa)[ፋይል ፎቶ - አሶሽየትድ ፕረስ/AP]
የአርበኞት ግንቦት ሰባት መሪ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ አሜሪካ በሚገኘው መኖርያቸው በልዊስበርግ (Lewisburg, Pa)[ፋይል ፎቶ - አሶሽየትድ ፕረስ/AP]

የአርበኞት ግንቦት ሰባት መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ብረስልስ ቤልጄም በሚገኘዉ የአዉሮፓ ፓርላማ በኢትዮጽያ ስለተከሰተዉ ድርቅና ረሃብ ማብራሪያ መስጠታቸዉ ታዉቋል።

የኢትዮጵያን መንግሥት በትጥቅ ከሥልጣን የማዉረድ ዓላማ ያነገበዉን ግንቦት ሰባት በመምራት በጎሬቤት ኤርትራ እንደሚገኙ የሚታወቀዉ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ስብሰባዉን ባዘጋጁት የፓርላማዉ አባላት እንደተጋበዙ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ አሁን በድርቅ ምክንያት ስለተከሰተዉ የምግብ እጥረት ያደረጉት ንግግርም ድርቅ ተፈጥሮአዊ ክስተት፣ ረሃብ ግን የመንግስት የኢኮኖሚ ፖሊሲ ዉድቀት መሆኑን የሚያመለክት ነዉ ብለዋል።

“ከኢትዮጵያ ረሃብን ማስወገድ ከባድ አይደለም” ያሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ፤ መንግሥት ሁሉን ነገር የመቆጣጠር አባዜ ይዞታል፣ገበሬዉን መፈናፈኛ አሳጥቶ ከእለት ጉርስ ያለፈ የኢኮኖሚ ሕይወት እንዳይኖረዉ አድጓል” ብለዋል፡፡ አያይዘውም እየጨመረ የሄደዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛትና እንዲሁም ፤ ኬሚካል ማዳበሪያ እየፈጠረ ያለዉ ችግር እንደ ምግብ እጥረት ምክንያትነት ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የአሁኑን ድርቅ ኢልኒኖ የተባለዉ የአየር መዛባት እንዳስከተለዉና እስካሁን ድርቁ ባሰከተለዉ ረሃብ የሞተ ሰዉ እንደሌለ ለአስቸኳይ ጊዜ የመደበዉን ርዳታም ድርቅ ላጠቃዉ ሕዝብ እያደለ መሆኑን ይናገራል።

የአርበኞች ግንቦት ሰባት መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የዛሬዉ የአዉሮፓ ሕብረት ንግግራቸዉ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ፓለቲካ ጉዳዮችም ላይ ያተኮረ መሆኑን ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ለለዉጥ አሻፈረኝ በማለት ተቃዋሚዎች ጋር የገባዉ ፍጥጫ ለአዉሮፓ ሕብረት አሳሳቢ በመሆኑ አባላቱ ሰለ ወቅታዊ የአገሪቱ የፓለቲካ ሁኔታም እንደተወያዩ ተናግረዋል።

ቃለ-ምልልሱን ለመስማት የተያያዘውን የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

የአርበኞች ግንቦት ሰባት መሪ ለአዉሮፓ ፓርላማ ንግግር አደረጉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:02 0:00

XS
SM
MD
LG