ዋሽንግተን ዲሲ —
በኢትዮጵያ በሚገኙ ቁርጥ ግብር ከፋይ ነጋዴዎች ላይ የተደረገው አዲስ የቀን ገቢ ግምት ያስነሳው የተቃውሞ ሥራ ማቆም አድማ ቀጥሏል። በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ነጋዴዎች ተቃውሟቸውን ለመግለፅ ያደረጉት ሥራ የማቆም ዐድማ ዛሬ ሦስተኛ ቀኑን አስቆጥሯል።
አዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ የሚገኙ ነጋዴዎች ቅሬታቸውን በጹሑፍ አቅርበው ምላሽ እየጠበቁ እንደሆነ ገልፀውልናል።
የመንግሥት ባለሥልጣናቱ ግብር መክፈል ግዴታ መሆኑን ገልፀው ቅሬታ ያለው አካል ቅሬታውን አግባብ ባለው መልኩ ያቅርብ ብለዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ