ዋሽንግተን ዲሲ —
በኦሮሚያ ክልል የቀን ገቢ ግምት መጨመር ጋር በተያያዘ የተነሳው ሥራ የማቆም አድማ ተቃውሞ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉን ነዋሪዎች ይናገራሉ። በትናንትናው ዕለት በአምቦና በወሊሶ ከተማ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች፤ አድማው በዛሬው ዕለትም መቀጠሉን ይናገራሉ። በወሊሶና በአምቦ ከተማ ዛሬም የንግድ ቤቶች ተዘግተው ትራንስፖርትም ተቋርጦ መዋሉን ተናግረዋል።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኮሙዩንኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ አምቦ፣ወሊሶ፣ ጊንጪና ደንቢ ዶሎ አካባቢ አድማ መኖሩን አረጋግጠው ሌሎች አካባቢዎች ግን በሰላማዊ መንገድ ሂደቱ እየተከናወነ ነው ብለዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ