No media source currently available
በትግራይ ክልል በወረዳ ራያ ዓዘቦ የሚኖር ህዝብ ለከባድ የንጹህ የመጠጥ ውሃ ችግር ተጋልጠናል ይላል። ይህንን ችግር ለማቃለል ተብለው የተቆፈሩ የውሃ ጉድጓዶችም ኣገልግሎት መስጠት እንዳልጀመሩ ህዝቡ ይናገራል። በወረዳው በሓደ ኣልጋ ቀበሌ የዳላተ የገጠር መንደር የሚኖሩ ኣቶ ሕሉፍ ገብረሚካኤልና ጎረቤቶቻው በንጹህ የመጠጥ ውሃ እጦት እንደተሰቃዩ አጽንኦት ሰጥተው ገልፀዋል።