አዲስ አበባ —
አቃቤ ሕግ ከአንድ አመት በፊት እነ ዘላለም ወርቅ አገኘሁ በሚል የክስ መዝገብ በቀድሞ የአንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ አመራር አባላት አቶ ሃብታሙ አያሌዉና አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የአረና ፓርቲ የአመራር አባል አቶ አብረሃ ደስታ በሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባል አቶ የሺዋስ አሰፋና አቶ አብረሃም ሰለሞን ላይ በሽብር ወንጀል በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስራ ዘጠነኛ ወንጀል ችሎት ክስ መስርቶባቸዉ ሲከራከሩ ቆይተዋል።
ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ባለፈዉ ነሀሴ 14 ቀን 2007 በሰጠዉ ዉሳኔ አምስቱ ተከሳሾች አቃቤ ሕግ የመሰረተባቸዉን የሽብር ወንጀል መከላከል ሳያስፈልጋቸዉ በነጻ እንዳሰናበታቸዉ ይታወሳል።
ሙሉን ዘገባ መለስካቸው አምሃ ከአዲስ አበባ አጠናቅሮ ልኮልናል የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያድምጡ።