No media source currently available
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በቀድሞ የአንድነት ፓርቲ አመራር በእነ አቶ ሃብታሙ አያሌዉና ሌሎች አራት ተከሳሾች ጉዳይ ላይ ብይን ለማሰማት ለሁለተኛ ጊዜ ሌላ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ። ፍርድ ቤቱ ከብሔራዊ ደህንነት የተገኙ ናቸዉ የተባሉ መረጃዎችን በጥሬአቸዉ እንዲቀርቡ ዛሬ አቃቤ ሕግን አዟል።