በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመጣጣኝ የዉክልና ምርጫ ሥርዓት ዉይይት እንዲደረግ ይሁንታ አለ ተባለ


ፋይል ፎቶ - ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ
ፋይል ፎቶ - ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ኢዴፓን ጨምሮ ስምንት ፓርቲዎች አባል ከሆኑበት አገር አቀፍ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት አባላት ጋር ሰሞኑን ተወያይተዋል።

ተመጣጣኝ የዉክልና ሥርዓት በሚባለዉ የፓርላማ ምርጫ ሥርዓት ላይ ዉይይት እንዲደረግ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ፈቃደኛ መሆናቸዉን አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ተናገሩ።

የኢትዮጵያዉያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኢዴፓ ፕሬዚደንት ዶክተር ጫኔ ከበደ ለአሜሪካ ድምጽ እንዳስረዱት የተለያዩ ፓርቲዎች የፓርላማ ዉክልና እንዲኖራቸዉ የሚያስችለዉ ይህ ስርዓት እስከ ሕዝብ ተወካዩች ምክር ቤት ድረስ ዉይይት ሊደረገበት እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተሰፋ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢዴፓን ጨምሮ ስምንት ፓርቲዎች አባል ከሆኑበት አገር አቀፍ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምክር ቤት አባላት ጋር ሰሞኑን ተወያይተዋል።

እስክንድር ፍሬዉ የኢዴፓዉን መሪ አነጋግሮ ዘግቧል የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያድምጡ።

ተመጣጣኝ የዉክልና ምርጫ ሥርዓት ዉይይት እንዲደረግ ይሁንታ አለ ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:26 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG