አዲስ አበባ —
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የቀድሞ አመራር አባል ሃብታሙ አያሌውና ሌሎች ተከሣሾች ጠበቃና አቃቤ ሕግ ሊያደርጉት የነበረው ክርክር ለሌላ ቀን ተቀጥሯል።
ፌደራሉ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ጉዳዩን ዛሬ ያልሰማውና የቀጠረው እሥረኞች ተሟልተው ባለመቅረባቸው እንደሆነ መናገሩ ተገልጿል።
የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ተከሣሾቹ ከእሥር እንዲፈቱ አስተላልፎት የነበረው ውሣኔ መታገዱ ፍርድ ቤት የሚያቀርብ ጉዳይ ነው ተብሏል።
የድምጽ ፋይሉን በመጫን ዝርዝሩን ከመለስካቸው አምሃ ዘገባ ያድምጡ።