የቀድሞ የአንድነት ለዴሞክራዊና ለፍትህ ፓርቲ አመራር አባል አቶ ሃብታሙ አያሌዉን ጨምሮ በሌሎች አራት የተቃዋሚ ፓርት አመራሮች ክስ ላይ የበታች ፍርድ ቤት የሰጠዉን ብይን አስመልክቶ አቃቤ ሕግ ላቀረበዉ የይግባኝ አቤቱታ የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬም ዉሳኔ እንዳልሰጠ አስታወቀ።
ፍርድ ቤቱ ዛሬ ዉሳኔ ሊሰጥ ያልቻለዉ የታችኛዉ ፍርድ ቤት ብይን የሰጠበት መዝገብና አቃቤ ያቀረባቸዉ ማስረጃዎች ስላልደረሱት መሆኑን ገልጿል። መዝገቡ እንዲመጣም ትእዛዝ ሰጥቷል። ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በዚህ ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ሲቀጥር ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ሲሆን፣ ዉሳኔዉን ጥቅምት 29 ቀን ለማሰማት ቀጠሮ ሰጥቷል።
አቃቤ ሕግ የቀድሞ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአመራር አባላት የነበሩትን አቶ ሃብታሙ አያሌዉና አቶ ዳንኤል ሺበሺ የአረናዉ አቶ አብረሃ ደስታ፣ የሰማያዊዉ አቶ የሺ ዋስ አሰፋ እንዲሁም አቶ አብረሃም ሰለሞን ላይ የሽብር ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዉ ቢሆንም የፌደራሉ ከፍተና ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ከሱን ሊያስረዳ አልቻልም ሲል መከላከል ሳያስፈልጋቸዉ በነጻ እንዲሰናበቱ መወሰኑ ይታወሳል።
ሙሉውን ዝርዝር ለመስማት የተያያዘውን የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።