በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተቃዋሚ መሪዎች ችሎት ለአራተኛ ጊዜ ተቀጠረ


የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ-ሰሚ ችሎት በአምስቱን የተቃዋሚ መሪዎች ላይ ለቀረበዉ ከስ ለአራተኛ ጊዜ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ።

የቀድሞ የአንድነት ለፍትህና ሌዴሞክራሲ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረዉ ሀብታሙ አያሌው፥ የአረና ትግራይ ምክትል የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረዉ አብረሃ ደስታና ሌሎች ሶስት የተቃዊሚ ፓርቲዎች አመራር አባላት ባለፈዉ ዓመት ሰኔ ወር በሽብር ተከሰዉ እንደነበር አይዘነጋም።

ባለፈዉ ነሐሴ ወር ግን የታችናዉ ፍርድ ቤት አቃቤ ሕግ ለወንጀሉ በቂ ማስተጃ አላቀረበም በማለት በነጻ እንደለቀቃቸዉ ይታወሳል። አቃቤ ሕግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ባቀረበዉ ይግባኝ አምስቱም ተቀካሾች አሁንም በእስር ይገኛሉ። የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ችሎቱን ያልሰማበትን ምክንያት አላብራራም ሆኖም ጉዳያቸዉ ለሚመጣዉ ሰኞ ተቀጥሯል።

መለስካቸዉ አመሃ የላከዉን ዘገባ የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያድምጡ።

የተቃዋሚ መሪዎች ችሎት ለአራተኛ ጊዜ ተቀጠረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:02 0:00

XS
SM
MD
LG