በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በበርበራ ጉዳይ የአፍሪካ ቀንድ ውዝግብ ቀጥሏል

በበርበራ ጉዳይ የአፍሪካ ቀንድ ውዝግብ ቀጥሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:51 0:00

በበርበራ ጉዳይ የአፍሪካ ቀንድ ውዝግብ ቀጥሏል

ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ በአፍሪካ ቀንድ ውጥረት የቀሰቀሰውን የባሕር በር መግባቢያ ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ የሚስተዋሉ ለውጦችና ክስተቶች እንደቀጠሉ ነው።

ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ በወታደራዊ ትብብር፣ ኤርትራና ሶማሊያ ደግሞ በሰሞኑ የመግባቢያ ሰነድ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

ኤርትራ ለሶማሊያ ሉዓላዊነት፣ አንድነትና የግዛት አሃድነት እውቅና እንደምትሰጥ ያሳወቀች ሲሆን ጂቡቲ የሰሞኑ ሁኔታ እንዳሳሰባቸው የገለፁ አካላትን ተቀላቅላለች።

በሌላ በኩል የሰነዱን መፈረም ከተከተለው ውዝግብ ጋር በማኅበረሰቦች መካከል መካረር የመፈጠሩ አዝምሚያ በተለይም የስደተኞች ደኅንነት ጉዳይ እንደሚያሳስበው የኦሮሞ ውርስ፣ አመራርና ተሟጋች ማኅበር የሚባል ቡድን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ከሶማሊላንድ ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ሜጀር ጄኔራል ኑህ ኢስማኤል ታኒ ጋር ሰኞ፣ ታኅሳስ 29/2016 ዓ.ም. በወታደራዊ ትብብር ዙሪያ መወያየታቸው ተገልጿል።

አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደው በዚህ ውይይት ላይ ሁለቱ ባለሥልጣናት መመካከራቸውን ያስታወቀው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በማኅበራዊ መገናኛ ገፁ ባወጣው መረጃ ነው።

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼኽ መሀሙድ ደግሞ በኤርትራ ጉብኝት አድርገው ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተወያይተዋል።

ሀሰን ሼኽ መሀሙድ ከኤርትራ አቻቸው ጋር ያደረጉትን ውይይት በተመለከተ ከኤርትራ ቴሌቪዥን ባደረጉት ቃለ ምልልስ “ኤርትራ ለሶማሊያ ሉዓላዊነት፣ አንድነትና የግዛት አሃድነት ድጋፍ እንዳላት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ እንዳረጋገጡላቸው” የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር በኤክስ ገፁ ላይ አስፍሯል።

“ኤርትራን በተደጋጋሚ ጎብኝቻለሁ። ለኛ ኤርትራ ቤታችን ናት” ያሉት ፕሬዚዳንት መሀሙድ “አሁን የመጣነው ኤርትራ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገችልን ባለችበት በዚህ ወቅት ሶማሊያ እየተካሄደባት ባለው ሽብር ላይ ስለያዘችው ጦርነት ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ ለመግለፅ ነው” ማለታቸውንም አትቷል። ስለቀጣናው የቅርብ ጊዜ ተለዋዋጭነትም መወያታቸውን ገልጸዋል፡፡

“ኤርትራ የሶማሊያን ሉዓላዊነት፣ አንድነትና የግዛት አሃድነት ለማስጠበቅ ድጋፍ ስታደርግ ቆይታለች፤ ይህም የኤርትራ ዓለምአቀፍ አቋም ነው” ካሉ በኋላ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ ዛሬም ይህን እንዳረጋገጡላቸው ገልፀዋል።

ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ዛሬ ሞቃዲሾ ተመልሰዋል።

ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ ኢትዮጵያ ወደቧን የምትጠቀመው ጂቡቲ በሶማልያና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ውጥረት እንዳሳሰባትና በአፅንዖት እየተከታተለችው እንደሆነ መግለጿን አዣንስ ፍራስ ፕሬስ ዘግቧል። መንግሥቷ ትናንት ባወጣው መግለጫ “ሁኔታውን ለማርገብ በሁለቱ ሃገሮች መካከል ውይይት እንዲደረግ” አሳስቧል።

የቀጣናው የጋራ ልማት ትብብር ድርጅት (ኢጋድ) የወቅቱ መሪ የሆነችው ጂቡቲ "የኢጋድ አባል ሀገሮች በሙሉ የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት መከበር አለበት" የሚል አቋም እንዳላትም ገልፃ ቀውሱን ለመፍታት ከአባል ሀገሮች ጋር ሆና ጥረት እያደረገች መሆኗንም አስታውቃለች።

“ጉዳዩ አሳስቦናል፤ የሶማሊያ ሉዓላዊነት መከበር አለበት” እያሉ መግለጫ ከሰጡ የዓለምአቀፍ ማኅበረሰብ አባላት መካከል ዩናይትድ ስቴትስ፣ የአፍሪካ ኅብረት፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ የእሥላማዊ ትብብር ድርጅትና የአረብ ሊግም ይገኛሉ።

በሌላ በኩል የመግባቢያ ስምምነቱን ተከትሎ በተቀናቃኝ ኃይሎች መካከል እየተስተዋሉ ያሉ ጫና የመፍጠር እንቅስቃሰሴዎች ቀጣናዊ ውጥረትን ሊያባብሱ እንደሚችሉ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች መምህርና ተመራማሪ ሱራፌል ጌታነህ፣ ጠቁመዋል።

አሁን ያለው ውጥረት በድርድር እልባት ካላገኘ ከቀጣናው ያለፈ ቀውስ ሊፈጥር ይችላል የሚል ሥጋት እንዳላቸው ሱራፌል ጠቅሰው ዓለምአቀፍ ተቋማት ችግሩን ለመፍታት የሚጠቅባቸውን ሚና መጫወት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ከሦስት አሥርት ዓመታት በላይ በሃርጌሳ ላይ እምብዛም ሥልጣን የሌላት ሞቃዲሾ ለኢትዮጵያ በሊዝ ኪራይ የባሕር በር፣ ለሶማሊላንድ ደግሞ በሂደት የነፃ ሀገርነት ዕውቅናን ከኢትዮጵያ እንድታገኝ ያስችላል የተባለው አወዛጋቢ ስምምነት ተግባራዊ እንዳይሆን ዓለምአቀፍ ድጋፍ ግፊቷን ቀጥላለች።

ስምምነቱ በሶማሊያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አሃድነት ላይ የተቃጣ “ግልፅ ወረራ” እንደሆነ የገለፁት የሶማልያው ፕሬዚዳንት ሞሀሙድ፣ ስምምነቱን “ውድቅ የሚያደርግ” ያሉትን ሕግ እንደፈረሙም አስታውቀዋል።

ፕሬዚዳንቱ በኤክስ ገፃቸው ላይ “ይህ ህግ በዓለምአቀፍ ሕግ መሠረት አንድነታችንን፣ ሉዓላዊነታችንንና የግዛታችንን አሃድነት ለመጠበቅ ያለንን ቁርጠኛነት የሚያሳይ ነው” ብለዋል።

በሌላ በኩል “በዚህ ስምምነት የሚጎዳ አካልም ሆነ ሀገር የለም” ያለችው ኢትዮጵያ፣ የመግባቢያ ስምምነቱን በመፈረሜ “የተጣሰ ሕግ የለም” ማለቷ ይታወቃል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሠነዱ መፈረም የፈጠረው ውጥረት በማኅበረሰቦች መካከል መካረር እንዳያስከትልና በተለይም የስደተኞች ደኅንነት እንደሚያሠጋው የኦሮሞ ውርስ አመራርና ተሟጋች ማኅበር የሚባል ዋና ፅህፈት ቤቱ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኝ ቡድን ትናንት ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

በእንግሊዝኛ ስሙ መጠሪያ ምኅፃር ኦ-ላ (OLLAA) እየተባለ የሚጠራው ማኅበር ሶማሊላንድ ከአሥሮች ዓመታት እራሷን ማስተዳደር በኋላ ስላላት ዕውቅና የማግኘት ፍላጎት፣ የኢትዮጵያን የባህር በር ማግኘት አስፈላጊነትና የሶማሊያን የሉዓላዊነትና የግዛት አሃድነት መጠበቅ ሥጋት ጉዳይ ጎን ለጎን እንደሚገነዘብ አመልክቶ “የሁሉንም ወገኖች ፍላጎቶች የሚመልስ ሚዛናዊ መፍትኄ ቁልፍ ነው” ብሏል።

ይሁንና በማኅበራዊ ሚድያ ላይ እየወጡ ያሉ ፀረ-ኦሮሞ ስሜቶችና በስደተኞች ላይ ያሉ የጥላቻ ንግግሮች በብርቱ እያሰጉት እንደሆነ ኦ-ላ (OLLAA) አመልክቶ ስደተኞች ሊከበሩ እንደሚገባና በዓለምአቀፍ ህግም ጥበቃ እንደሚደረግላቸው አስታውሷል።

የሶማሊላንድና የሶማሊያ መንግሥታትም በከለላቸው ሥር ደኅንነትን ለጠየቁ ኦሮሞዎችና ሌሎችም ጥበቃ እንዲያደርጉ ማኅበሩ ጥሪ አቅርቧል።

ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ በኢትዮጵያና በሶማሊያ መንግሥታት መካከል የሚደረጉ ድርድሮችን እንዲደግፍና ሶማልያ የሚገኘው የመንግሥታቱ ድርጅት የስደት ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቢሮም እየተሰሙ ባሉ ንግግሮች ውስጥ የስደተኞች ደኅንነት መጠበቁን እንዲያረጋግጥ ኦ-ላ ጠይቋል።

ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ በአፍሪካ ቀንድ ውጥረት የቀሰቀሰውን የባሕር በር መግባቢያ ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ የሚስተዋሉ ለውጦችና ክስተቶች እንደቀጠሉ ነው።

ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ በወታደራዊ ትብብር፣ ኤርትራና ሶማሊያ ደግሞ በሰሞኑ የመግባቢያ ሰነድ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

ኤርትራ ለሶማሊያ ሉዓላዊነት፣ አንድነትና የግዛት አሃድነት እውቅና እንደምትሰጥ ያሳወቀች ሲሆን ጂቡቲ የሰሞኑ ሁኔታ እንዳሳሰባቸው የገለፁ አካላትን ተቀላቅላለች።

በሌላ በኩል የሰነዱን መፈረም ከተከተለው ውዝግብ ጋር በማኅበረሰቦች መካከል መካረር የመፈጠሩ አዝምሚያ በተለይም የስደተኞች ደኅንነት ጉዳይ እንደሚያሳስበው የኦሮሞ ውርስ፣ አመራርና ተሟጋች ማኅበር የሚባል ቡድን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ከሶማሊላንድ ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ሜጀር ጄኔራል ኑህ ኢስማኤል ታኒ ጋር ሰኞ፣ ታኅሳስ 29/2016 ዓ.ም. በወታደራዊ ትብብር ዙሪያ መወያየታቸው ተገልጿል።

አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደው በዚህ ውይይት ላይ ሁለቱ ባለሥልጣናት መመካከራቸውን ያስታወቀው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በማኅበራዊ መገናኛ ገፁ ባወጣው መረጃ ነው።

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼኽ መሀሙድ ደግሞ በኤርትራ ጉብኝት አድርገው ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተወያይተዋል።

ሀሰን ሼኽ መሀሙድ ከኤርትራ አቻቸው ጋር ያደረጉትን ውይይት በተመለከተ ከኤርትራ ቴሌቪዥን ባደረጉት ቃለ ምልልስ “ኤርትራ ለሶማሊያ ሉዓላዊነት፣ አንድነትና የግዛት አሃድነት ድጋፍ እንዳላት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ እንዳረጋገጡላቸው” የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር በኤክስ ገፁ ላይ አስፍሯል።

“ኤርትራን በተደጋጋሚ ጎብኝቻለሁ። ለኛ ኤርትራ ቤታችን ናት” ያሉት ፕሬዚዳንት መሀሙድ “አሁን የመጣነው ኤርትራ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገችልን ባለችበት በዚህ ወቅት ሶማሊያ እየተካሄደባት ባለው ሽብር ላይ ስለያዘችው ጦርነት ለፕሬዝዳንት ኢሳያስ ለመግለፅ ነው” ማለታቸውንም አትቷል። ስለቀጣናው የቅርብ ጊዜ ተለዋዋጭነትም መወያታቸውን ገልጸዋል፡፡

“ኤርትራ የሶማልያን ሉዓላዊነት፣ አንድነትና የግዛት አሃድነት ለማስጠበቅ ድጋፍ ስታደርግ ቆይታለች፤ ይህም የኤርትራ ዓለምአቀፍ አቋም ነው” ካሉ በኋላ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ ዛሬም ይህን እንዳረጋገጡላቸው ገልፀዋል።

ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ዛሬ ሞቃዲሾ ተመልሰዋል።

ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ ኢትዮጵያ ወደቧን የምትጠቀመው ጂቡቲ በሶማሊያና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ውጥረት እንዳሳሰባትና በአፅንዖት እየተከታተለችው እንደሆነ መግለጿን አዣንስ ፍራስ ፕሬስ ዘግቧል። መንግሥቷ ትናንት ባወጣው መግለጫ “ሁኔታውን ለማርገብ በሁለቱ ሃገሮች መካከል ውይይት እንዲደረግ” አሳስቧል።

የቀጣናው የጋራ ልማት ትብብር ድርጅት (ኢጋድ) የወቅቱ መሪ የሆነችው ጂቡቲ "የኢጋድ አባል ሀገሮች በሙሉ የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት መከበር አለበት" የሚል አቋም እንዳላትም ገልፃ ቀውሱን ለመፍታት ከአባል ሀገሮች ጋር ሆና ጥረት እያደረገች መሆኗንም አስታውቃለች።

“ጉዳዩ አሳስቦናል፤ የሶማሊያ ሉዓላዊነት መከበር አለበት” እያሉ መግለጫ ከሰጡ የዓለምአቀፍ ማኅበረሰብ አባላት መካከል ዩናይትድ ስቴትስ፣ የአፍሪካ ኅብረት፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ የእሥላማዊ ትብብር ድርጅትና የአረብ ሊግም ይገኛሉ።

በሌላ በኩል የመግባቢያ ስምምነቱን ተከትሎ በተቀናቃኝ ኃይሎች መካከል እየተስተዋሉ ያሉ ጫና የመፍጠር እንቅስቃሴዎች ቀጣናዊ ውጥረትን ሊያባብሱ እንደሚችሉ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች መምህርና ተመራማሪ ሱራፌል ጌታነህ፣ ጠቁመዋል።

አሁን ያለው ውጥረት በድርድር እልባት ካላገኘ ከቀጣናው ያለፈ ቀውስ ሊፈጥር ይችላል የሚል ሥጋት እንዳላቸው ሱራፌል ጠቅሰው ዓለምአቀፍ ተቋማት ችግሩን ለመፍታት የሚጠቅባቸውን ሚና መጫወት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ከሦስት አሥርት ዓመታት በላይ በሃርጌሳ ላይ እምብዛም ሥልጣን የሌላት ሞቃዲሾ ለኢትዮጵያ በሊዝ ኪራይ የባሕር በር፣ ለሶማሊላንድ ደግሞ በሂደት የነፃ ሀገርነት ዕውቅናን ከኢትዮጵያ እንድታገኝ ያስችላል የተባለው አወዛጋቢ ስምምነት ተግባራዊ እንዳይሆን ዓለምአቀፍ ድጋፍ ግፊቷን ቀጥላለች።

ስምምነቱ በሶማሊያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አሃድነት ላይ የተቃጣ “ግልፅ ወረራ” እንደሆነ የገለፁት የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሀሙድ፣ ስምምነቱን “ውድቅ የሚያደርግ” ያሉትን ሕግ እንደፈረሙም አስታውቀዋል።

ፕሬዚዳንቱ በኤክስ ገፃቸው ላይ “ይህ ህግ በዓለምአቀፍ ሕግ መሠረት አንድነታችንን፣ ሉዓላዊነታችንንና የግዛታችንን አሃድነት ለመጠበቅ ያለንን ቁርጠኛነት የሚያሳይ ነው” ብለዋል።

በሌላ በኩል “በዚህ ስምምነት የሚጎዳ አካልም ሆነ ሀገር የለም” ያለችው ኢትዮጵያ፣ የመግባቢያ ስምምነቱን በመፈረሜ “የተጣሰ ሕግ የለም” ማለቷ ይታወቃል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሠነዱ መፈረም የፈጠረው ውጥረት በማኅበረሰቦች መካከል መካረር እንዳያስከትልና በተለይም የስደተኞች ደኅንነት እንደሚያሠጋው የኦሮሞ ውርስ አመራርና ተሟጋች ማኅበር የሚባል ዋና ፅህፈት ቤቱ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኝ ቡድን ትናንት ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

በእንግሊዝኛ ስሙ መጠሪያ ምኅፃር ኦ-ላ (OLLAA) እየተባለ የሚጠራው ማኅበር ሶማሊላንድ ከአሥሮች ዓመታት እራሷን ማስተዳደር በኋላ ስላላት ዕውቅና የማግኘት ፍላጎት፣ የኢትዮጵያን የባህር በር ማግኘት አስፈላጊነትና የሶማሊያን የሉዓላዊነትና የግዛት አሃድነት መጠበቅ ሥጋት ጉዳይ ጎን ለጎን እንደሚገነዘብ አመልክቶ “የሁሉንም ወገኖች ፍላጎቶች የሚመልስ ሚዛናዊ መፍትኄ ቁልፍ ነው” ብሏል።

ይሁንና በማኅበራዊ ሚድያ ላይ እየወጡ ያሉ ፀረ-ኦሮሞ ስሜቶችና በስደተኞች ላይ ያሉ የጥላቻ ንግግሮች በብርቱ እያሰጉት እንደሆነ ኦ-ላ (OLLAA) አመልክቶ ስደተኞች ሊከበሩ እንደሚገባና በዓለምአቀፍ ህግም ጥበቃ እንደሚደረግላቸው አስታውሷል።

የሶማሊላንድና የሶማሊያ መንግሥታትም በከለላቸው ሥር ደኅንነትን ለጠየቁ ኦሮሞዎችና ሌሎችም ጥበቃ እንዲያደርጉ ማኅበሩ ጥሪ አቅርቧል።

ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ በኢትዮጵያና በሶማሊያ መንግሥታት መካከል የሚደረጉ ድርድሮችን እንዲደግፍና ሶማሊያ የሚገኘው የመንግሥታቱ ድርጅት የስደት ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቢሮም እየተሰሙ ባሉ ንግግሮች ውስጥ የስደተኞች ደኅንነት መጠበቁን እንዲያረጋግጥ ኦ-ላ (OLLAA) ጠይቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG