የሶማሊላንዱ የመከላከያ ሚኒስትር አብዲቃኒ ሞሃሙድ አቲዬ አገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር የወደብ እና የባሕር ኃይል ሠፈር ለመመሥረት የመግባቢያ ሰነድ መፈረሟን በመቃወም ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን አስታውቀዋል።
የመከላከያ ሚኒስትሩ ትናንት ከፕሬዝደንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸውን እና በስምምነቱ ላይ የተለያየ ሃሳብ እንዳላቸው አስታውቀዋል።
ስልጣን የለቀቁበት ምክንያትም አገሪቱ ከኢትዮጵያ ጋር ከፈረመችው የመግባቢያ ሰነድ ጋር በቀጥታ እንደሚገናኝ የመከላከያ ሚኒስትሩ ለአገር ውስጥ ቴሌቪዥን ገልጸዋል።
“ስምምነቱን እቃወማለሁ፣ አልቀበለውም” ሲሉ ተደምጠዋል የመከላከያ ሚኒስትሩ።
ዓለም አቀፍ እውቅና የሌላትን እና ከ30 ዓመታት በላይ በራስ ገዝነት የቆየችውን ሶማሊላንድ፣ ሶማሊያ አሁንም እንደግዛቷ ትቆጥራታለች፡፡ ከኢትዮጵያ ጋር የፈረመችውን ስምምነትም ሶማሊያ ተቃውማለች፡፡ ተቃውሞዋን ለማስመዝገብም አምባሳደሯን ከአዲስ አበባ ጠርታለች፡፡
የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሃሳን ሼክ ሞሃሙድ ስምምነቱን ውድቅ የሚያደርግ ያሉትን ሕግ በትናንትናው ዕለት ፈርመዋል።
መድረክ / ፎረም