በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሊያው ፕሬዝደንት አሥመራ ናቸው


የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሃሳን ሼክ ሞሃሙድ አስመራ፣ ኤርትራ
የኤርትራ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሃሳን ሼክ ሞሃሙድ አስመራ፣ ኤርትራ

የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሃሳን ሼክ ሞሃሙድ ለሁለት ቀናት ጉብኝት ዛሬ እኩል ቀን አሥመራ ገብተዋል።

ፕሬዝደንቱ እና ልዑካቸው አሥመራ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ፣ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ሁለቱ ፕሬዝደቶች የሁለቱን አገራት ግንኙነት በሚያጠናክሩበት እንዲሁም ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮችን በተመለከተ እንደሚወያዩ የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በ‘X’ ማኅበራዊ መድረክ ላይ ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ባለፈው ሳምንት የወደብ እና የባሕር ኃይል ሠፈር ለመመሥረት የመግባቢያ ሰነድ መፈረማቸውን ተከትሎ፣ የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሃሳን ሼክ ሞሃሙድ በትናንትናው ዕለት ስምምነቱን ውድቅ የሚያደርግ ያሉትን ሕግ ፈርመዋል።

የመግባቢያ ስምምነቱ ኢትዮጵያ ቀይ ባሕር ላይ በር እንዲኖራትና በበርበራ ወደብ ላይም ለንግድ እና ለባሕር ኃይል እንቅስቃሴ የሚውል 20 ኪ.ሜ. የሚሆን ቦታ ለ50 ዓመታት በሊዝ እንደምታገኝ አመልክቷል።

ከ30 ዓመታት በላይ በራስ ገዝነት የቆየችውን ሶማሊላንድ፣ ሶማሊያ እንደግዛቷ የምትቆጥራት ሲሆን፣ ዓለም ዓቀፍ እውቅናም የላትም።

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ አገራቸው የቀይ ባሕር በር እንደሚያስፈልጋት መግለጻቸውንና ከሶማሊላንድ ጋርም የመግባቢያ ሥምምነት መፈረማቸውን ተከትሎ፣ በአካባቢው ውጥረት እንደስፈነ እና አዲስ ግጭትም እንዳያስከተል ሥጋት መፍጠሩ በመዘገብ ላይ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG