በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በበርበራ ጉዳይ የአፍሪካ ቀንድ ውዝግብ ቀጥሏል


በበርበራ ጉዳይ የአፍሪካ ቀንድ ውዝግብ ቀጥሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:51 0:00

ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ በአፍሪካ ቀንድ ውጥረት የቀሰቀሰውን የባሕር በር መግባቢያ ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ የሚስተዋሉ ለውጦችና ክስተቶች እንደቀጠሉ ነው።

ኢትዮጵያና ሶማሊላንድ በወታደራዊ ትብብር፣ ኤርትራና ሶማሊያ ደግሞ በሰሞኑ የመግባቢያ ሰነድ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

ኤርትራ ለሶማሊያ ሉዓላዊነት፣ አንድነትና የግዛት አሃድነት እውቅና እንደምትሰጥ ያሳወቀች ሲሆን ጂቡቲ የሰሞኑ ሁኔታ እንዳሳሰባቸው የገለፁ አካላትን ተቀላቅላለች።

በሌላ በኩል የሰነዱን መፈረም ከተከተለው ውዝግብ ጋር በማኅበረሰቦች መካከል መካረር የመፈጠሩ አዝምሚያ በተለይም የስደተኞች ደኅንነት ጉዳይ እንደሚያሳስበው የኦሮሞ ውርስ፣ አመራርና ተሟጋች ማኅበር የሚባል ቡድን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ ከሶማሊላንድ ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ሜጀር ጄኔራል ኑህ ኢስማኤል ታኒ ጋር ሰኞ፣ ታኅሳስ 29/2016 ዓ.ም. በወታደራዊ ትብብር ዙሪያ መወያየታቸው ተገልጿል።

አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደው በዚህ ውይይት ላይ ሁለቱ ባለሥልጣናት መመካከራቸውን ያስታወቀው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በማኅበራዊ መገናኛ ገፁ ባወጣው መረጃ ነው።

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼኽ መሀሙድ ደግሞ በኤርትራ ጉብኝት አድርገው ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተወያይተዋል።

ሀሰን ሼኽ መሀሙድ ከኤርትራ አቻቸው ጋር ያደረጉትን ውይይት በተመለከተ ከኤርትራ ቴሌቪዥን ባደረጉት ቃለ ምልልስ “ኤርትራ ለሶማሊያ ሉዓላዊነት፣ አንድነትና የግዛት አሃድነት ድጋፍ እንዳላት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ እንዳረጋገጡላቸው” የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር በኤክስ ገፁ ላይ አስፍሯል።

XS
SM
MD
LG