በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤርትራዊ ጋዜጠኛ አማኑኤል አስራት በፔን ኢንትርናሽናል ተሸለመ


ኤርትራዊው ጋዜጠኛና ገጣሚ አማኑኤል አስራት የዚህ ዓመት ፔን ኢንተርናሽናል ተሸላሚ
ኤርትራዊው ጋዜጠኛና ገጣሚ አማኑኤል አስራት የዚህ ዓመት ፔን ኢንተርናሽናል ተሸላሚ

ላለፉት አስራ አራት ዓመታት ኤርትራ ዉስጥ ታስሮ የሚገኘዉ ጋዜጠኛ አማኑኤል አስራት የፔን ኢንተርናሽናል ተሸላሚ ሆኗል። ባለፈዉ ጥር ስድስት ሄግ ዉስጥ በተካሄደ ሥነ-ስርዓት ጋዜጠኛ አማኑኤል አስራት ለመናገር መብት ከታገሉ አንዱ በመባል ከግብጽ ከቱርክና ጋዜጠኞች ጋር የዓመቱ የፔን ተሸላሚ ሆኗል።

የታገደዉ ዘመን የተባለዉ የኤርትራ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረዉ አማኑኤልአስራት እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር ከእአአ 2001 ዓመተ ምህረት ጀምሮ በአገሪቱ እስር ቤትዉስጥ ነዉ የሚገኘዉ።

ሄግ ዉስጥ የሚገኘዉ Writers Unlimited Interantaoal የተባለዉ ከጋዜጠኞች መብት አስከባሪ ድርጅት Pen International ጋር በመተባበርየሚሰራዉ ዓለም አቀፍ ድርጅት ባዘጋጀዉ ስነስርዓት ከዓመቱ የፔን ተሸላሚዎች አንዱሆኖአል።

በፔን ኢንተርናሽናል (Freedom to Write) የተባለዉ ፕሮግራም ዳይሬክተር አን ሃሪሰን(Ann Harrison) ለዜጠኛ አማኑኤል አስራት የዓለም አቀፉ ድርጅት ሽልማት የሰጠበትን ምክንያት ሲገልጹ ኤርትራ ዉስጥ ያለዉ የመናገርና የመጻፍ መብት እጅግ አሳሳቢ ሆኔታ ላይ የሚገኝ መሆኑን ገልጸዋል።

ኤርትራዊው ጋዜጠኛና ገጣሚ አማኑኤል አስራት በፔን/ኦክስፋም በተዘጋጀው ዓመታዊ ጀግና ጸሃፊ በመባል ተሰየመ
ኤርትራዊው ጋዜጠኛና ገጣሚ አማኑኤል አስራት በፔን/ኦክስፋም በተዘጋጀው ዓመታዊ ጀግና ጸሃፊ በመባል ተሰየመ

ጋዜጠኛዉ ጋዜጠኛ አማኑኤል አስራት ከአስራ አራት ዓመት በፊት የተሰወረ መሆኑን ጠቅሰዉ ይሙት ይኑር ባይታወቅም ለእርሱ ይህን ሽልማት በመስጠት በአገሪቱ ዉስጥ ምንም የመናገር የመጻፍ መብት እንደሌለ ልናሰምርበት ነዉ ብለዋል።

የድምጽ ፋይሉን በመጫን ሙሉዉን ዘገባ ያድምጡ።

ኤርትራዊ ጋዜጠኛ አማኑኤል አስራት በፔን ኢንትርናሽናል ተሸለመ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:45 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG