ዋሽንግተን ዲሲ —
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የፍትህ ጋዜጣ፣ የአዲስ ታይምስና የፋክት መጽሔት ባለቤት እና አዘጋጅ በነበረበት ወቅት በጹሑፍ ሥራዎቹ "በሀሰት ወሬ መንዛት" በሚል ክስ ቀርቦበትና “ጥፋተኛ” ተብሎ የተፈረደበትን የሦስት ዓመት እስራት ለመጨረስ በዝዋይ ማረሚያ ቤት ይገኛል።
በዚህ ማረሚያ ቤት ከታሰረ ሁለት ዓመት ከሦስት ወር እንዳስቆጠረ ቤተሰቦቹ ይናገራሉ። የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንደም አላምረው ደሳለኝ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገረው፤ በዛሬው ዕለት ዝዋይ እስር ቤት ወንድሙን ፍለጋ የሄደው ለመሞከር እንጂ አገኘዋለሁ በሚል ተስፋ አልነበረም።
ጽዮን ግርማ የጋዜጠኛ የመስገን ደሳለኝን እናትና ወንድሙን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።