ዋሺንግተን ዲሲ —
የተመስገን ወንድሞችና አንድ የቤተሰቡ ወዳጅ ካለፈው ሣምንት ረቡዕ ጀምሮ በተለያዩ ጊዜአት ተመስገን ታስሮ ወደሚገኝበት ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እየተመላለሱ ሊያገኙት እንዳልቻሉ፣ ይዘውት የሄዱት ስንቅም መመለሱን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡
ቤተሰቦቹ ወደ ፍትሕ ሚኒስቴርም ሄደው ጠቅላይ አቃቤ ሕጉን ማግኘታቸውንና የፌደራል ማረሚያ ቤቶችን የኮምዩኒኬሽንስ ዳይሬክተርን ፀሐፊያቸው ጋ ሆነው ለሦስት ሰዓታት ጠብቀው ሳያገኟቸው መቅረታቸውንም አመልክተዋል፡፡
የፌደራል ማረሚያ ቤቶች የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ መንግሥቴ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ጉዳዩ ለእርሣቸው አዲስ እንደሆነና የሚያውቁት ተመስገን የሚገኘው ዝዋይ ማተሚያ ቤት ውስጥ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ተመስገን እሥራት ላይ ያለው የፍትሕ ጋዜጣ፣ የአዲስ ታይምስና የፋክት መፅሔቶች ባለቤትና አዘጋጅ ተመስገን ደሣለኝ የሁለት ዓመት ከሁለት ወር እሥራት ተፈርዶበት መሆኑ ይታወቃል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡