በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የት ነው ያለው?” ቤተሰቦቹ ይጠይቃሉ


ተመስገን ደሣለኝ - የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ
ተመስገን ደሣለኝ - የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ

የእሥራት ፍርዱን እየፈፀመ ያለው የፍትሕ ጋዜጣ፣ የአዲስ ታይምስና የፋክት መጽሔት አዘጋጅና አሣታሚ ተመስገን ደሣለኝ የት እንደሚገኝ ማወቅ ከተሳናቸው ዘጠኝ ቀናት እንዳለፈ ቤተሰቦቹ ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ። የጋዜጠኞች ደህንነት ተሟጋቹ ድርጅት ሲ.ፒ. ጄ የኢትዮጵያ መንግሥት ተመስገን ያለበትን ማሳወቅ ብቻ ሳይሆን መፍታትም ጭምር አለበት ብሏል።

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ ተመስገንን ለመጠየቅ ዝዋይ እስር ቤት መመላለስ ከጀመሩ ዘጠኝ ቀናት መቆጠሩን ገልፆ “ተመስገን እዚህ የለም” የሚል ምላሽ ከማግኘት ውጪ ተጨማሪ ምላሽ ማግኘት እንዳልቻሉ ተናግሯል።

የጋዜጠኞች ደህንነት ተሟጋቹ ድርጅት ሲ.ፒ. ጄ የምስራቅ አፍሪካ ተጠሪ ሙረቲ ሙቲጋ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤተሰብን ስጋት መስማታቸውን ገልፀው ጉዳዩም በጣም እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል።

ጽዮን ግርማ ያጠናቀረችውን ዘገባ ለማድመጥ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ይጫኑ።

“ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የት ነው ያለው?” ቤተሰቦቹ ይጠይቃሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:27 0:00

XS
SM
MD
LG