በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፑቲን የዩክሬን ጦርነት ሰላማዊ ዜጎች ለከፍተኛ ጥቃት የተጋለጡ መሆኑን ሂዩማን ራይት ዎች ገለጸ


ፕሬዚዳንት ፑቲን በምስራቅ ዩክሬን ላይ ወታዳራዊ ጥቃት እንዲካሄድ መወሰናቸውን ተከትሎ ሰላማዊ ዜጎችና ህጻናት የዩክሬንና የፖላንድን ድንበር እያቋረጡ ነው እኤአ የካቲት 24/2022 ሮይተርስ
ፕሬዚዳንት ፑቲን በምስራቅ ዩክሬን ላይ ወታዳራዊ ጥቃት እንዲካሄድ መወሰናቸውን ተከትሎ ሰላማዊ ዜጎችና ህጻናት የዩክሬንና የፖላንድን ድንበር እያቋረጡ ነው እኤአ የካቲት 24/2022 ሮይተርስ

ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ድርጅት ሂዩማን ራይት ዋች የሩሲያው ፕሬዚዳንት ለዩክሬን ያቀዱት የጦር እቅድ የሰላማዊ ዜጎችንና የሰላማዊ ዜጎችን መሰረተ ልማት ሆን ብሎ በማውደም የዩክሬንን የመከላከል አቅም የማዳከም ስልትን ያካተተ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የሂዩማን ራትይ ዎች ዋና ሥራ አስፈጻሚ ድሬክተር ኬኒት ሮዝ፣ የሩሲያ ጦር የሶሪያን መንግሥት የአገሪቱን የመጨረሻ አማጽያንን በሰሜን ክፍለ ግዛት ኢድልብ እንዲቆጣጠር በማገዝ የተጠቀመበትን ስልት በዩክሬንም እንደሚደግመው ተናግረዋል፡፡

የሩሲያ ጦር በተደጋጋሚ ከሚያደርጋቸው ውጊያዎች የተሰናዳው ዝርዝር ጥናት እንደሚያሳየው የሩሲያ ጦር ሆን ብሎ የሰላማዊ ተቋማትን እንደሚያጠቃ ገልጸዋል፡፡ ሆስፒታሎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የገበያ ስፍራዎችና የሰላማዊ ሰዎች ህንጻዎች ያለምህረት ይጠቃሉ ሲሉም ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም

“እንደሚመስለኝ የወታደራዊ ጥቃት ኢላማ የሆኑ ወደ 43 ክስተቶችን የመዘግብን ይመስለኛል፡፡ የሶሪያ አማጽያን ያለምንም ከልካይ ሰተት ብለው እንዲገቡ በሲቪል ተቋማትን ላይ ሆን በማጥቃት ከጥቅም ውጭ እንዲሆኑ በማድረግ በኢዲልብ ለሚገኙ ወደ ሶስት ሚሊዮን ለሚሆኑ ሰላማዊ ዜጎች ህይወት የማይቻል እንዲሆን ተደርጓል፡፡” ብለዋል፡፡

ሮዝ “ከዚህ ውስጥ የተለየ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ቢኖር ከዚህ ድርጊት በስተጀርባ ባለው የአስፈጻሚው ትዕዛዝ ሰንሰለት ሆን ተብሎ የሚፈጸመው የሩሲያ ህግ ወጥ ፖሊሲ ነው” ብለዋል፡፡

“ፕሬዚዳንት ፑቲን ራሳቸው በግል ትዕዛዝ የመስጠት ድርሻ ኃላፊነት ያላቸው መሆኑን ደርሰንበታል፡፡” ያሉት ሮዝ “ከዚያም አልፈን እነዚያ የቦምብ ድብደባዎች በተካሄዱ ጊዜ የድብደባዎቹ አስፈጻሚ የነበሩት ሁለት ሰዎች የሩሲያ ጀግና የተባለው ሽልማት የተሰጣቸው መሆኑን አስተውለናል፡፡ ስለዚህ ስጋታችን አሁንም ይህ ነገር ይደገማል የሚል ነው፡፡” ብለዋል፡፡

ሮዝ ይህ የሩሲያ ጦር ይህን የጦርነት ስትራቴጂ በዚህኛው ጦርነት እንዳይደግሙት ጠንካራ ግፊት ሊደረግባቸው ይገባል ይላሉ፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው የሩሲያ ዋንቶን በኢድሊብ የሚያደርገውን የጦር አውሮፕላን ድብደባው ያቋረጠው እኤአ በ2020 በጀርመን ፈረሳይና ቱርክ በጋራ በተካሄደበት ግፊት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ስለሆነም በፑቲን ላይ የሚደረገው ዓለም አቀፍ ጫና አሁንም መቀጠል ያለበት መሆኑን የሂዩማን ራትይ ዎች ዋና ሥራ አስፈጻሚ ድሬክተር ኬኒት ሮዝ፣ አሳስበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG