በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬን የበረራ መስመሯን ለሲቪል መንገደኞች ዝግ ማድረጓን አስታወቀች


ዩክሬኖች እናት ሃገር ሃውልት እያሉ የሚጠሩት ሃውልትን ከከተማጋ ጋር የሚያሳይ ፎቶ/ በፌብሩዋሪ 13/ 2022 የተነሳ
ዩክሬኖች እናት ሃገር ሃውልት እያሉ የሚጠሩት ሃውልትን ከከተማጋ ጋር የሚያሳይ ፎቶ/ በፌብሩዋሪ 13/ 2022 የተነሳ

ዩክሬን ከፍተኛ የደህንነት ሥጋት መኖሩን ተከትሎ የበረራ መስመሯን ለሲቪል መንገደኞች ዝግ ማድረጓን አስታውቃለች።

የዩክሬን የአየር ትራፊክ አገልግሎት በድህረ ገፁ ላይ ባሰፈረው መልዕክት የሀገሪት በረራ መስመሮች ከእኩለ ለሊት ጀምሮ ዝግ ሆነዋል፣ የአየር ትራፊክ አገልግሎትም በጊዜያዊነት ተቋርጧል።

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቩለድሚር ዚለንስኪ ከዛሬ ጀምሮ በሀገሪቱ ሙሉ የአስቸኳይ ግዜ ያወጁ ሲሆን ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጋር መነጋገራቸውን በመግለፅ ህዝቡ እንዳይፈራና እንዳይደናገጥ አሳስበዋል።

ዩናይትድ ስቴትስና ሌሎች የዩክሬን የምዕራብ አጋር ሀገራት በዚህ ሳምንት የሩሲያ ባለሥልጣናትና የሀገሪቱ የገንዘብ ሥርዓት ላይ ማዕቀብ የጣሉ ሲሆን ሩሲያ ጀምራው የነበረውን የነዳጅ ቱቦ የመዘርጋት ፕሮጀክትም አቋርጠዋል። በቀጣይ ሩሲያ ለሚኖራት እንቃስቃሴም ከዚህ የከፋ እርምጃ እንደሚወስዱ አስታውቀው ነበር።

XS
SM
MD
LG